ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና ሩዋንዳ የኢኮኖሚ ውህደት ማዕቀፍ ለመጀመር ተስማሙ
16:45 02.08.2025 (የተሻሻለ: 16:54 02.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና ሩዋንዳ የኢኮኖሚ ውህደት ማዕቀፍ ለመጀመር ተስማሙ
ሀገራቱ ሰኔ 27 ቀን በፈረሙት የሰላም ስምምነት መሠረት፤ የቀጣናዊ ኢኮኖሚ ውህደት ማዕቀፍ መርሆዎች ላይ መገባባታቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ገልጿል፡፡
ሀገራቱ በኃይል፣ በመሠረተ ልማት፣ በማዕድን ቁፋሮ፣ በብሔራዊ ፓርክ አስተዳደር፣ በቱሪዝም እና በሕብረተሰብ ጤና በመተባበር በምሥራቅ እና በመካከለኛው አፍሪካ ቀጣና የኢኮኖሚ እድገትን ያፋጥናሉ ሲል መግለጫው አመላክቷል፡፡
የሰላም ስምምነቱ ትግበራ ተቆጣጣሪ የጋራ ኮሚቴ የመጀመሪያ ስብሰባን ተከትሎ ባወጣው መገለጫ፤ "የደህንነት እና ኢኮኖሚያዊ ትብብርን ለማስቀጠል ትርጉም ያላቸው እርምጃዎችን እየወሰዱ ነው" ብሏል፡፡
በሳምንቱ ዋሽንግተን ላይ የተደረጉ ስብሰባዎች ዓላማዎች፦
🟠 በደህንነት ጉዳዮች ቅንጅትን ማጠናከር፣
🟠 የረጅም ጊዜ መረጋጋት እና ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ፣
🟠 በቀጣናው ያለውን "የላቀ ኢኮኖሚያዊ አቅም" ማውጣት፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia
/