የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ለቀጣናዊ የልማት ትብብር ማስተሳሰሪያ ሆኖ እያገለገለ ነው ተባለ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ለቀጣናዊ የልማት ትብብር ማስተሳሰሪያ ሆኖ እያገለገለ ነው ተባለ
የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ለቀጣናዊ የልማት ትብብር ማስተሳሰሪያ ሆኖ እያገለገለ ነው ተባለ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 02.08.2025
ሰብስክራይብ

የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ለቀጣናዊ የልማት ትብብር ማስተሳሰሪያ ሆኖ እያገለገለ ነው ተባለ

የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር እ.አ.አ ከ2025 እስከ 2028 የሦስት ዓመታት የስትራቴጂክ ዕቅድ አዘጋጅቷል፡፡ 

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ሥሜ፤ "የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር የሀገራቱ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ቀጣናዊ የልማት ትብብር ማስተሳሰሪያ ገመድ ሆኖ እያገለገለ ነው" ማለታቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡

የመተላለፊያ ጊዜን በመቀነስና አቅምን በማሳደግ ቀጣናዊ ውህደትና የልማት ትብብርን በማስፋት የንግድ ሥርዓትን እያቀላጠፈ መሆኑንም አንስተዋል።

ስትራቴጂክ ዕቅዱ “የባቡር መሠረተ ልማት ለንግድና ቀጣናዊ ትስስር” በሚል መሪ ሐሳብ የኢትዮጵያና የጅቡቲ መንግሥታት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0