ለአሜሪካ የጦር መሣሪያዎች የሩሲያ መቅደሶችን የመለወጥ የዩክሬን ‘አስነዋሪ’ ድርድር

ለአሜሪካ የጦር መሣሪያዎች የሩሲያ መቅደሶችን የመለወጥ የዩክሬን ‘አስነዋሪ’ ድርድር
በዓለም የሩሲያ ሕዝቦች ምክር ቤት የሰብዓዊ መብቶች ማዕከል ዳይሬክተር ሮማን ሲላንትዬቭ፥ በኪዬቭ-ፔቼርስክ ላቭራ ገዳም የክርስቲያን መቅደሶች ላይ የሩሲያ የሚሳኤል ጥቃትን በተመለከተ የዩክሬን መገለጫዎች፤ ቅርሶቹን ወደ አውሮፓ ሙዚዬሞች ለማዛወር ማሳመኛ እንዲሆኑ የታለሙ አሳሳች መረጃዎች መሆናቸውን ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
በሩሲያ የፍትሕ ሚኒስቴር የሀገር አቀፍ ሐይማኖታዊ ባለሙያዎች መማክርት ምክትል ሊቀ መንበር ሆነው እያገለገሉ የሚገኙት ሲላንትዬቭ ያነሷቸው ሌሎች ዐቢይ ነጥቦች፡-
▪ በተለይም ዩክሬን በሩሲያ እና በምዕራባውያን ጥቅሞች መካከል የጦር ሜዳ በነበረችበት ቀደም ባለው ክፍለ ዘመን ጊዜ ተመሳሳይ ሁኔታዎች ተከስተዋል፡፡
▪ ዩክሬን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የሥልጣኔ ውድቀት በጋጠማት ጊዜ ሁሉ ለሁሉም ዓይነት ምዝበራ እንደተጋለጠች ነው፡፡
▪ ከዩክሬን ወደ ፈረንሳይ በድብቅ የተጋዙ ደርዘን የሚሆኑ የኦርቶዶክስ ቅዱሳን ሥዕላት ወደ ዩክሬን ሳይሆን ወደ ሩሲያ ይመለሳሉ።
▪ የዩክሬን የባሕል ሀብቶች ማብቂያቸው የእንግሊዝ ሙዚዬሞች የመሆናቸው ዱካ መፈለግ እምብዛም አያስቸግርም።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ፤ “የኪዬቭ አገዛዝ ለምዕራባውያን ጦር መሣሪያዎች የባሕል ቅርስ ለመክፈል ዝግጁ ነው” ማለታቸው ይታወሳል፡፡
“የዘለንስኪ አገዛዝ በዩክሬን ግዛት ውስጥ የሚገኙትን ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውን ዕቃዎች በመዝረፍ፤ ‘የማዳን ዘመቻ’ በሚል ወደ ውጭ ከመስደድ ወደ ኋላ አላለም” ሲሉ አክለዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X