የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በ2018 በጀት ዓመት ከኤሌክትሪክ የወጪ ንግድ 427 ሚሊየን ዶላር እንደሚጠበቅ አስታወቀ
13:12 02.08.2025 (የተሻሻለ: 13:14 02.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በ2018 በጀት ዓመት ከኤሌክትሪክ የወጪ ንግድ 427 ሚሊየን ዶላር እንደሚጠበቅ አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በ2018 በጀት ዓመት ከኤሌክትሪክ የወጪ ንግድ 427 ሚሊየን ዶላር እንደሚጠበቅ አስታወቀ
ኢትዮጵያ ከፍተኛ የውሃ እና የታዳሽ የኃይል አቅሟን በመጠቀም ለጎረቤት ሀገራት ቀልጣፋ እና ዘላቂ የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ በምሥራቅ አፍሪካ የኃይል ገበያ ውስጥ ትልቅ ሚና እየተጫወተች መሆኑ ነው ተቋሙ ያስታወቀው፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ሞገስ መኮንን የኢትዮጵያ የኃይል ኤክስፖርት ቀጣናዊ ውህደት እና የኢኮኖሚ ዕድገት እያመጣ መሆኑን ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡
የባለፉት ዓመታት ከኃይል ሽያጭ የውጭ ምንዛሪ ገቢ፦
በ2023 100 ሚሊየን ዶላር፣
በ2024 140 ሚሊየን ዶላር፣
በ2025 የዳታ ማይኒንግ ገቢን ጨምሮ 330 ሚሊየን ዶላር ደርሷል።
በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከ165.9 ሚሊየን ዶላር እቅድ ውስጥ 118 ሚሊየን ዶላር (71 በመቶ) ማሳካት መቻሉን አብራርተዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X