አፍሪካውያን ሴቶች የሚገባቸውን ቦታ እስኪያገኙ ትግላቸውን መቀጠል አለባቸው - መዓዛ አሸናፊ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአፍሪካውያን ሴቶች የሚገባቸውን ቦታ እስኪያገኙ ትግላቸውን መቀጠል አለባቸው - መዓዛ አሸናፊ
አፍሪካውያን ሴቶች የሚገባቸውን ቦታ እስኪያገኙ ትግላቸውን መቀጠል አለባቸው - መዓዛ አሸናፊ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 02.08.2025
ሰብስክራይብ

አፍሪካውያን ሴቶች የሚገባቸውን ቦታ እስኪያገኙ ትግላቸውን መቀጠል አለባቸው - መዓዛ አሸናፊ

አፍሪካውያን ሴቶች የማሕበረሰባቸው ምሰሶ ናቸው ያሉየቀድሞ የኢትዮጵያ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት፤ በአንድ ሀገር ኢኮኖሚ፣ ማሕበራዊ እና ፖለቲካ ሕይወት ውስጥ የሚጫወቱት ወሳኝ ሚና እንዳላቸው ለስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ተናግረዋል።

"ብዙ ፈተናዎች አሉ፤ ኢኮኖሚያዊ፣ ማሕበራዊ ፈተናዎች አሉ። ጎጂ ባሕላዊ ልማዶች አሁንም አሉ። ነገር ግን ሴቶች ከትምህርት፣ ከአመራር እና ከኢኮኖሚ ተሳትፎ አንፃር ቀስ በቀስ አየተለወጡ ነው። መሻሻሎች አሉ ግን የተዘጋ ጉዳይ አይደለም። ሂደቱ አሁንም መቀጠል አለበት።"

ልክ እንደቀደመው ትውልድ አፍሪካውያን ሴቶች ተደራጅተው ትግላቸውን መቀጠል አለባቸው፣

የአፍሪካ ሴቶች የሕዝቡን 50 በመቶ ይወክላሉ፤ ስለዚህም ሴቶች 50 በመቶ ውክልና ያስፈልጋቸዋል፣

ከፖለቲካዊ ሹመት በተጨማሪ ሴቶች በአከባቢያዊ አስተዳደር እና በሁሉም የውሳኔ መስጪያ ቦታዎች ውክልና ያስፈልጋቸዋል ሲሉም አክለዋል።

የአፍሪካ ሴቶች ቀን ሐምሌ 24 ተከብሮ ውሏል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0