በጊኒ ኮናክሪ በተከሰተው ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ በትንሹ 10 ሰዎች ሞቱ
17:27 01.08.2025 (የተሻሻለ: 19:54 01.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በጊኒ ኮናክሪ በተከሰተው ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ በትንሹ 10 ሰዎች ሞቱ
መንግሥት ባወጣው መግለጫ ረቡዕ ምሽት የዘነበዉ ከባድ ዝናብ በከተማዋ ከፍተኛ የንብረት ውድመት አድርሷል ሲል ገልጿል።
መግለጫው አክሎም “ለተጎጂ ቤተሰቦች እና ለተፈናቀሉ ሰዎች አስፈላጊውን እርዳታ እንዲያደርጉ እንዲሁም የመከላከል እና የአደጋ ጊዜ ምላሽ እርምጃዎችን እንዲያጠናክሩ ለሚመለከታቸው ባለሥልጣናት ትዕዛዝ ተሰጥቷል” ብሏል።
የሀገሪቱ የሜትሮሎጂ ኤጀንሲ እንዳስታወቀው ከፍተኛ ነጎድጓዳማ ዝናብ እስከ ቅዳሜ ድረስ በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች የሚቀጥል ሲሆን ኮናክሪ እና ሌሎች በርካታ ከተሞች በብዛት ሊጠቁ እንደሚችሉ አስጠንቅቋል።
ኤጀንሲው “በእነዚህ አካባቢዎች ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ ሊከሰት ይችላል” ሲል አሳስቧል።
ባለንበት ወር በምዕራብ አፍሪካ ከፍተኛ ዝናብ የተመዘገበ ሲሆን ይህም በሴኔጋል፣ በጋምቢያ እና በጊኒ የጎርፍ አደጋ አስከትሏል።
ከማህበራዊ የትስስር ገጾች የተገኙ ቪዲዮዎች
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia

1/3
© telegram sputnik_ethiopia

2/3
© telegram sputnik_ethiopia

3/3
© telegram sputnik_ethiopia
1/3
© telegram sputnik_ethiopia
2/3
© telegram sputnik_ethiopia
3/3
© telegram sputnik_ethiopia