የብሪታንያ ጨለማ ታሪክ፦ የሕዝቦች ባሕላዊ ቅርሶች ስልታዊ ዝርፊያ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየብሪታንያ ጨለማ ታሪክ፦ የሕዝቦች ባሕላዊ ቅርሶች ስልታዊ ዝርፊያ
የብሪታንያ ጨለማ ታሪክ፦ የሕዝቦች ባሕላዊ ቅርሶች ስልታዊ ዝርፊያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.08.2025
ሰብስክራይብ

የብሪታንያ ጨለማ ታሪክ፦ የሕዝቦች ባሕላዊ ቅርሶች ስልታዊ ዝርፊያ

ዩናይትድ ኪንግደም ከእስያ እና ከመካከለኛው ምስራቅ ባሕላዊ ቅርሶችን በመዝረፍ የነበራት ታሪካዊ ሚና “በሀገራት ታሪካዊ ትውስታ ላይ የተፈጸመ ስልታዊ ወንጀል” ነው ሲሉ ኢራናዊው የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ምሁር ሩሆላ ሞዳበር ተናግረዋል።

ሞዳበር ለስፑትኒክ በሰጡት አስተያየት፤ ዩኬ ለዘመናት የቆየ ታሪካዊ ማንነት እንደሌላት ስለሚሰማት፤ ይህን ክፍተት ለመሙላት ስትል ሆን ብላ በዋጋ የማይተመኑ ባሕላዊ ቅርሶችን ስትዘርፍ ቆያታለች ብለዋል።

አክለውም ዋና ዋናዎቹ የብሪታኒያ ሙዚዬሞች በቅኝ ግዛት መስፋፋትና ወታደራዊ ወረራዎች ወቅት የተዘረፉ እጅግ ብዙ ቅርሶችን ሰብስበዋል። ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ ባላት ተፅዕኖ፤ በተለይም በዓለም አቀፍ ሕግ ውስጥ ያሉ ክፍተቶችን በመጠቀም እንዲህ ያለው ስርቆት በሂደት ሕጋዊ ተደርጎ ቆይቷል ሲሉ አብራርተዋል፡፡

ሞዳበር እ.ኤ.አ በ1970 የወጣው የዩኔስኮ ኮንቬንሽን፤ በወቅቱ በተፀዕኖ ወይም በቅኝ ገዥዎች ቁጥጥር ስር የነበሩ የአካባቢው ባለሥልጣናት ቅርሶቹ እንዲወጡ ከፈቀዱ በውጭ እንዲቆዩ እንደሚያስቀምጥ ተናግረዋል።

ለአብነትም ከኢራን የተወሰደውን የኮሂኖር አልማዝ እንዲሁም ከፐርሰፖሊስ እና ሃማዳን ካሉ ታሪካዊ ቦታዎች የተሰረቁ በሺዎች የሚቆጠሩ ቅርሶችን ጠቅሰዋል።

ሞዳበር እነዚህ ቅርሶች ተራ ቁሶች ሳይሆኑ የማንነት፣ የታሪክ እና የባሕል ሉዓላዊነት ምልክቶች ናቸው ብለዋል።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0