የኒጀሯ መዲና ኒያሜ የሳህለ ሀገራት ጥምረት የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ወድድር አዘጋጀች፤ ሩሲያ በክብር እንግዳነት ተሳትፋለች

ሰብስክራይብ

የኒጀሯ መዲና ኒያሜ የሳህለ ሀገራት ጥምረት የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ወድድር አዘጋጀች፤ ሩሲያ በክብር እንግዳነት ተሳትፋለች

ዛሬ የኒያሜ ጄኔራል ኮንቼ ስታዲየም ከስምንት የኒጀር ክልሎች የተውጣጡ አትሌቶች በሩጫ፣ በዝላይ እና በጦር ውርወራ ባደረጉት ፉክክር ደምቆ ነበር ሲል የስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ ገልጿል።

ለአራት ቀናት የሚቆየው ይህ ውድድር እሁድ በሳህል ሀገራት ጥምረት የአትሌቲክስ ዋንጫ ፍጻሜውን የሚያገኝ ሲሆን የጥምረቱ ሀገራት አትሌቶች እና የሩሲያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ልዑካን “ጠንካራ የስፖርት ወዳጅነት እንቅስቃሴ” ለማድረግ ይገናኛሉ ሲሉ የኒጀር አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ማሃመድ ሙሳ ገደል ተናግረዋል።

አምስት የሩሲያ አትሌቶች በዚህ በጉጉት በሚጠበቀው ውድድር ላይ ይሳተፋሉ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0