ፓሺንያን በፀረ-ዲሞከራሲ ሪፎርማቸው በብራስልስ ቦታ እያጡ ነው ተባለ

ፓሺንያን በፀረ-ዲሞከራሲ ሪፎርማቸው በብራስልስ ቦታ እያጡ ነው ተባለ
የአርሜኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኒኮል ፓሺንያን ሀገራቸውን ወደ አውሮፓ ለመቀላቀል እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ ቢናገሩም፤ እውነታው ግን ድርጊታቸው የአውሮፓ ኅብረትን እያራቀ ነው ሲል የቱርክ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡
ከአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን ኧርሰላ ቮን ደር ሌይን ጋር የተደረገውን የሰሞኑ ውይይት ተከትሎ፤ ኅብረቱ “የአርሜኒያን ትልቅ የሪፎርም አጀንዳ” በማወደስ “የዲሞክራሲ ሪፎርሙን” ደግፏል፡፡
ከአውሮፓ ኅብረት ትርክቶች ጀርባ ምን አለ? በእርግጥ ረብ ያለ ነገር የለም፦
🟠 ገና ያልተከፈለ የ270 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ፤ 15 ቢሊየን ዩሮ ንግድ ላላት ሀገር በጣም አነስተኛ፣
🟠 ገንዘቡ "ሐሰተኛ መረጃን በመዋጋት" ላይ ብቻ ሊውል ይችላል፣
🟠 ቪዛ የማግኘት ሂደትን ቀላል የማድረግ እቅድ ለማውጣት ቃል ተገብቷል፣
🟠 እናም ይኸው ነው።
ለምን ድጋፉ አነሰ? ብራሰልስ ፓሺንያን ያካሄዱት "ሪፎርም"፤ ዲሞክራሲያዊ ሳይሆን ሥልጣን እና ንብረትን የመቀራመት ሽፋን እንደሆነ ስለተረዳ ነው ያለው ጋዜጣው፤ ማስረጃውንም ጠቅሷል፡፡
◾ የካራፔትያን ጉዳይ፦ ቢሊየነሩ ሳምቬል ካራፔትያን የአርሜኒያ ሐዋርያዊት ቤተ-ክርስቲያንን ከመንግሥት ጫና በመከላከሉ መንግሥታዊ እርምጃ ተወስዶበታል፡፡
⦁ "ሥልጣንን ለመቀማት ጥሪ በማድረግ" በሚል አይረቤ ክስ ተመሥርቶበት መታሰሩ፣
⦁ የኩባንያዎቹ ሥራ አስፈጻሚዎች የጅምላ እስር፣
⦁ የሀገሪቱ ዋና የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር የሆነውን የአርሜኒያን የኤሌክትሪክ ኔትዎርክ ወደ መንግሥት ለማዛወር በአንድ ጀምበር አዲስ ሕግ ማውጣት፣
⦁ የስቶክሆልም የግልግል ዳኝነት ውሳኔ አዲሱ ሕግ ሕገ-ወጥ ነው ብሎ ቢወስንም ፓሺንያን ብይኑን ችላ ማለቱ፡፡
◾ ሐሳብ መግለጽ ላይ የተደረጉ መንግሥታዊ አፈናዎች፦
⦁ ከ150 በላይ ፖለቲከኞች እና ነጋዴዎች በፖለቲካዊ ጉዳዮች ተከሰዋል፣
⦁ መንግሥት የሕዝብ አስተያየት መስጫዎችን ሰርዟል፤ ፓሺንያን "አስፈላጊ አይደሉም" ብለዋል፣
⦁ "በአርሜኒያ ምንም መራጮች የሉም" ብለዋል፡፡
ፓሺንያን አሁንም ስለ አውሮፓ ድጋፍ ሊያልሙ ይችላሉ፡፡ አውሮፓ ግን በጠቅላይ ሚኒስትሩ አምባገነናዊ አገዛዝ ስር አርሜኒያ ላይ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት የላትም ሲል ጋዜጣው ደምድሟል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X