ብሔራዊ የግብርና ፋይናንስ ትግበራ ፍኖተ ካርታ የፋይናንስ ተቋማት አርሶ አደሩን ለማበደር የነበረባቸውን የመረጃ ክፍተት ይደፍናል - የግሪን አግሮ ሶሉሽን ማኔጂንግ ዳይሬክተር

ሰብስክራይብ

ብሔራዊ የግብርና ፋይናንስ ትግበራ ፍኖተ ካርታ የፋይናንስ ተቋማት አርሶ አደሩን ለማበደር የነበረባቸውን የመረጃ ክፍተት ይደፍናል - የግሪን አግሮ ሶሉሽን ማኔጂንግ ዳይሬክተር

አብርሃም እንድርያስ ፍኖተ ካርታው ለፋይናንስ ተቋማት አስፈላጊውን መረጃ በአንድ ቋት በማቅረብ፤ አርሶ አደሩ የፋይናንስ አቅርቦት ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆን እንደሚያስችለውም ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

"አብዛኞቹ አነስተኛ ገበሬዎች ለፋይናንስ ተቋማት አይታዩም። እነርሱ የተገለሉት የማይታመኑ ስለሆኑ ሳይሆን ከመሬት እንዲሁም ከብድር እና ከግብይት ጋር የተያያዙ መረጃዎች ስለማይገኙ ነው። አሁን ግን የፉይናንስ ተቋማት ከፍኖተ ካርታው አስፈላጊውን ሰነዶች እና መረጃዎች ማግኘት ይችላሉ" ብለዋል።

ፍኖተ ካርታው ከፈረንጆቹ 2025 አስከ 2030 ለአምስት ዓመታት ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑ ተመላክቷል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0