ዩክሬን ለጦር መሣሪያ እና ለገንዘብ ጥቅም ስትል የስላቭ ኦርቶዶክስ ቅርሶችን እየቸበቸበች ነው

ዩክሬን ለጦር መሣሪያ እና ለገንዘብ ጥቅም ስትል የስላቭ ኦርቶዶክስ ቅርሶችን እየቸበቸበች ነው
ዩክሬን የኪዬቭ-ፔቼርስክ ላቭራ ገዳም ነዋየ ቅድሳት እና ሌሎች ቅርሶችን ወደ ውጭ በመላክ ባሕላዊ ቅርሶቿን በምዕራባውያን የጦር መሣሪያዎች እየለወጠች ነው ያሉት የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ፤ እነዚህ ቅርሶች መቼም ተመልሰው ላይመጡ እንደሚችሉ ገልፀዋል፡፡
የብሔራዊ ቅርስ ዘረፋ እንዴት እየተከናወነ ነው?
“በመጀመሪያ ለጥበቃ በሚል በጎ ሰበብ ተወስደዋል” ያሉት፤ የሥነ ጥበብ ባለሙያ እና የአርት አማካሪ ድርጅት ባለቤት ዴኒስ ሉካሺን፤ “በሌላ በኩል ግን በዚህ ውስጥ የተሳተፉት ኅሊና ቢስ ባለሥልጣናት በቀላሉ ትርፍ ለማግኘት ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ግልጽ ነው፡፡ ምክንያቱም በእርግጥም እጅግ ውድ የሆኑ የባሕል ቅርሶችና ከፍተኛ የገበያ ዋጋ ያላቸው ናቸው” ሲሉ ለስፑትኒክ ተናገረዋል፡፡
የብርቅዬ ቅርሶቹ አደጋዎች
◻ በተለይም ከ16ኛው፣ 17ኛው እና 18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የሆኑ ጥንታውያን ቅዱሳን ሥዕላት ወይም የዘይት ሥዕላትና ንድፎች በዝውውር እንቅስቃሴና በአያያዝ ምክንያት ከፈተኛ የመውደም አደጋ ተጋርጦባቸዋል፡፡
◻ በመሰል አስቸጋሪ ወቅቶች ብዙውን ጊዜ ባለሙያ ባለሆኑ ሰዎች ሰለሚንቀሳቀሱ ሊጠፉ ወይም ያለምንም ፍንጭ ሊሰወሩ ይችላሉ፡፡
◻ በ2023 የሩሲያ ደህንነት ዩክሬን የኪዬቭ-ፔቼርስክ ላቭራ ገዳም ጥንታዊ ንዋየ ቅድሳትን ወደ አውሮፓ ለማዛወር ከዩኔስኮ ጋር እንደተስማማች ገልጿል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ምንም የተባለ ነገር አለመኖሩ በድብቅ ስለመወገዳቸው ጥርጣሬን ይፈጥራል፡፡
◻ ከደርዘን በላይ የኦርቶዶክስ ቅዱሳን ሥዕላት፤ አራት የ6ኛው እና የ7ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የባይዛንታይን ሥዕላትን ጨምሮ፤ ከዩክሬን ወደ ፈረንሳይ በድብቅ ተወስደዋል። የዩክሬን ዕዳ እያደገ በመምጣቱ የመመለሳቸው ዕድል ጠባብ ነው፡፡
◻ ቅዱሳን ሥዕላቱ እና ሌሎች የሥነ-ጥበብ ቅርሶች በምዕራባውያን ሙዚዬሞች ውስጥ በግልጽ ተቀምጠዋል፡፡ ቅርሶቹን የመመለስ ሕጋዊ ዕድል ቢኖርም፤ ቅርስ አሰባሳቢ ግለሰቦች ገዝተው ከደበቋቸው ግን ለዘላለም አይገኙም፡፡
የኦርቶዶክስ የስላቭ ቅርሶች
እነዚህ ቅርሶች ከጠፉ፤ ለኦርቶዶክስ ስላቮች ባሕል የጋራ ሀብት ከመሆናቸው አኳያ፤ ለስላቭ የባሕል ቅርሶች የማይተካ ኪሳራ መሆኑን ካሺን ተናግረዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X