"በታሪክ ታላቁ የባሕል ዝርፊያ"፦ የግብጽ የቀድሞ የጥንታዊ ቅርሶች ሚኒስትር የእንግሊዞችን የጥንታዊ ቅርሶች ዝርፊያ አወገዙ

"በታሪክ ታላቁ የባሕል ዝርፊያ"፦ የግብጽ የቀድሞ የጥንታዊ ቅርሶች ሚኒስትር የእንግሊዞችን የጥንታዊ ቅርሶች ዝርፊያ አወገዙ
የግብጽ የቅርስ አሰሳ ተመራማሪ ዛሂ ሐዋስ ግብጽ በቅኝ ግዛት አገዛዝ ሥር በነበረችበት ወቅት የተዘረፉ ጥንታዊ ቅርሶችን በማስታወስ፤ የአውሮፓውያኑ የቅርስ ዘረፋ ለረጅም ጊዜ የዘለቀ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በፅሁፍ የተቀረፀው “የሮዜታ ድንጋይ” በዘውዳዊ ኃይል የተወሰደ ቢሆንም፤ የትኛውም የቅኝ ግዛት ኃይል የግብጽን ቅርስ የመውረስ መብት አልነበረውም" ሲሉ ለስፑትኒክ ተናግረዋል፡፡
ዓይን ካወጡ ድርጊቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦
🟠 በ1799 በፈረንሳይ ወታደሮች የተገኘው የሮዜታ ድንጋይ፤ ናፖሊዮ ከተሸነፈ በኋላ በእንግሊዞች ተወስዶ፤ ከ1802 ጀምሮ በለንደን ለዕይታ ቀርቧል፡፡
🟠 የቱታንክሃሙን መካነ መቃብር ቅርሶች፤ በቁፋሮው የገንዘብ ደጋፊ ሎርድ ካርናርቮን ተወስደዋል፡፡
🟠 እንግሊዛዊው አርኪኦሎጂስት ሃዋርድ ካርተር፤ 19 ቅርሶችን በድብቅ ወደ ኒውዮርክ ሜትሮፖሊታን የሥነ-ጥበብ ሙዚየም አስተላልፏል፡፡
🟠 ለሎርድ ካርናርቮን እና ለሥነ ግብጽ አጥኚው ጋርዲነር የተሰረቁ ጥንታዊ ቅርሶች በስጦታ ተሰጥቷቸዋል፡፡
🟠 ከቱታንክሃሙን መካነ መቃብር የሆነው የኔፈርቱም ሐውልት፤ በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ሌላ መካነ መቃብር ተወስዶ አሁን በለንደን ሙዚዬም ይገኛል፡፡
🟠 ከመሚዎች እስከ ፓፒረስ፤ የብሪቲሽ ሙዚዬም ሰባት አዳራሾቹን የሞላባቸው የግብጽ ቅርሶች፤ ሁሉም ያለ ግብጽ ይሁንታ የተወሰዱ ናቸው፡፡
ሐዋስ እና ሌሎች ምሁራን በእንግሊዝ ተቋማት ብቻ የሚገኙ 100 ሺህ የግብጽ ቅርሶች በአስቸኳይ እንዲመለሱ እና ለረጅም ጊዜ በቆየው የግብጽ ቅርስ ዘረፋ ዙሪያ ዓለም አቀፍ ውይይት እንዲደረግ ጥሪ እያቀረቡ ነው፡፡
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X