በአንጎላ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን ተከትሎ በተነሳው ሕዝባዊ ተቃውሞ በድምሩ 22 ሰዎች ተገደሉ

ሰብስክራይብ

በአንጎላ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን ተከትሎ በተነሳው ሕዝባዊ ተቃውሞ በድምሩ 22 ሰዎች ተገደሉ

በነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ምክንያት በታክሲ ሹፌሮች እንደተጀመረ የተዘገበው የሥራ ማቆም አድማ፤ በስድስት ግዛቶች ወደ ሕዝባዊ ተቃውሞ ተቀይሮ ለሁለት ቀናት ቆይቷል፡፡

የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰብሰባ ወቅት አለመረጋጋቱ ያስከተለውን ውጤት ይፋ አድርገዋል፦

◻ ከሟቾች ውስጥ ሥራ ላይ የነበረ አንድ ፖሊሲ ይገኝበታል፣

◻ 197 ሰዎች ተጎድተዋል፣

◻ ከ1 ሺህ 200 በላይ ሰዎች ታስረዋል፣

◻ የሠራተኞች እንቅስቃሴ እና የኢኮኖሚ ምርታማነት ተስተጓጉሏል፣

◻ በርካታ መደብሮች ተሰባብረዋል ወይም ተዘርፈዋል፤ አምቡላንሶች፣ አውቶብሶች እና የመንግሥት ተቋማትን ጨምሮ 25 ተሽከርካሪዎች ወድመዋል፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባን ተከትሎ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ባወጣው መግለጫ፤ “ወንጀለኛ ዓላማ ባላቸው ሰርጎ ገቦች” የተባባሱት ተቃውሞዎቹ፤ “ለሕዝብ ደህንነት እና ለማኅበራዊ ሰላም ስጋት” ወደመሆን መሸጋገራቸውን ገልጿል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በሀገሪቱ ዋና ከተማ ሉዋንዳ የሕዝብ ደህንነት እና ሰላም ወደነበረበት ተመልሷል፡፡

ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኙ ምሥሎች

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0