ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ በፀጥታና ደህንነት ዙሪያ ስምምነት ተፈራረሙ
16:34 31.07.2025 (የተሻሻለ: 16:44 31.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ በፀጥታና ደህንነት ዙሪያ ስምምነት ተፈራረሙ
የኢትዮጵያ እና የጂቡቲ መከላከያ ኮሚቴ አብረው በሚሠሯቸው የሠላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ መስማማታቸውን የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ውይይት የተደረገባቸው የስምምነቱ ጉዳዮች፦
የፀጥታና ደህንነት መረጃ ልውውጥ፣
ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን መግታት፣
ሽብርተኝነትን መከላከል፡፡
የመከላከያ ውጭ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክቶሬት ሜጄር ጄነራል ተሾመ ገመቹ፤ “በዚህ ቀጣና አብሮ እንደሚኖር ወዳጅ ሀገር፤ የጋራ ተጠቃሚነታችንን በሚያረጋግጡ ጉዳዮች ላይ በትብብር መሥራታችን በአካባቢው ያለውን ተግዳሮት አሸንፎ ለመውጣት የማይተካ ሚና አለው” ብለዋል።
በአዲስ አበባ ስምምነቱን የፈረሙት የጂቡቲ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም አማካሪ ኮሎኔል ማጆር አብዱረህማን አብዲ፤ ሁለቱ ሀገራት ያደረጉት ስምምነት ለቀጣናው የሚኖረው ፋይዳ የጎላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
