አርሶ እና አርብቶ አደሮች ያለ ተያዥ ከባንኮች ብድር የሚያገኙበት አሠራር አየተመቻቸ መሆኑን የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ ገለፁ

ሰብስክራይብ

አርሶ እና አርብቶ አደሮች ያለ ተያዥ ከባንኮች ብድር የሚያገኙበት አሠራር አየተመቻቸ መሆኑን የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ ገለፁ

ሚኒስትሩ ብሔራዊ የግብርና ፋይናንስ ትግበራ ፍኖተ ካርታ፤ ቋሚ ንብረታቸው ለተመዘገበ አርሶ እና አርብቶ አደሮች ሥራቸውን መደገፍ የሚያስችል የፋይናንስ አቅም እንደሚፈጥርም ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።

"ፋይናንስ ማለት ለአርሶ አደሩ ማዳበሪያ፣ ትራክተር እና ኮምባይነር የመግዣ ጉዳይ ነው። በዚህም ፍኖተ ካርታው አርሶ እና አርብቶ አደሩ የምርት ማሳደጊያ ግብዓቶችን በወቅቱ ገዝቶ መጠቀም እንዲችል እንዲሁም ወደ ሜካናይዜድ ግብርና እንዲገባ ትልቅ አቅም ይፈጥራል" ብለዋል።

ይፋ የተደረገው የግብርና ፋይናንስ ትግበራ ፍኖተ ካርታ በግብርና ሚኒስቴር እና በብሔራዊ ባንክ የጋራ ትብብር የተዘጋጀ ነው።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0