በእሳት መካከል ስኬታማ ቀዶ ሕክምና ያካሄዱት ኢትዮጵያውያን ሐኪሞች

ሰብስክራይብ

በእሳት መካከል ስኬታማ ቀዶ ሕክምና ያካሄዱት ኢትዮጵያውያን ሐኪሞች

ከሰሞኑን በወላይታ ሶዶ ኮምፕሪሄንሲቭ እና ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በተከሰተው የእሳት አደጋ ወቅት ዶ/ር ደመቀ ዳዊት እና የሕክምና ቡድን አባላት የቀዶ ሕክምና ሥራ ላይ ነበሩ፡፡

ዶ/ር ደመቀ ዳዊት "ከ2 ሰዓት በላይ የፈጀውን ከባድ የቀዶ ሕከምና አገልግሎት መስጠት ጀምረን እያለ ያላሰብነው ዱብዳ አጋጠመን፤ ቀሪዎቹን 40 ደቂቃዎች ሕንጻው እየተቃጠለም ቢሆን አማራጭ ስላልነበረ ለታካሚ ሕይወት ቅድሚያ ለመስጠት ወስነናል” ሲሉ ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ሁኔታውን አስረድተዋል፡፡

ዶ/ር ደመቀ፤ የሕክምና ሙያ ሥነ-ምግባር ከራስ ይልቅ ለታካሚ ሕይወት ቅድሚያ እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡

በጊዜው ሰመመን ውስጥ የነበሩት ታካሚ ያዕቆብ ቴጋ፤ ከአደጋው ለመትረፍ ምክንያት የሆኗቸውን የሕክምና ቡድን አባላት አመስግነው፣ "ፈጣሪ በጥበቡ ከአደጋው አውጥቶኛል" ሲሉም ነው የገለጹት፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0