ኢትዮጵያ እና አልጄሪያ በዓለም ዓቀፍ መድረኮች ላይ የጋራ አጀንዳዎችን ለማራመድ ከመግባባት ደረሱ
14:10 31.07.2025 (የተሻሻለ: 14:14 31.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ እና አልጄሪያ በዓለም ዓቀፍ መድረኮች ላይ የጋራ አጀንዳዎችን ለማራመድ ከመግባባት ደረሱ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ እና አልጄሪያ በዓለም ዓቀፍ መድረኮች ላይ የጋራ አጀንዳዎችን ለማራመድ ከመግባባት ደረሱ
ከፍተኛ የኢትዮጵያ ልዑክ በመምራት በአልጄሪያ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ከአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ እና በባሕር ማዶ የሚኖሩ ማኅበረሰብ ሚኒስትር አሕመድ አጣፍ ጋር መወያየታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ሚኒስትሮቹ በውይይታቸው በቅርቡ በአዲስ አበባ በተካሄደው የሁለቱ ሀገራት 5ኛው የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ወቅት መግባባት ላይ የተደረሰባቸውን ጉዳዮች የአፈፃፀም ሂደት ገምግመዋል፡፡
ሚኒስትሮቹ የተወያዩባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች፦
የኢትዮጵያ እና አልጄሪያን ስትራቴጂካዊ ትብብር ማሳደግ፣
በአፍሪካ እንዲሁም በዓለም ዓቀፍ መድረኮች የጋራ አጀንዳዎችን ማራመድ፣
ለአፍሪካ ኅብረት መጠናከር እና አፍሪካ በዓለም መድረክ ያላትን ሚና ማጎልበት፣
በንግድ፣ በኢንቨትመንት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በትምህርት መስኮች ግንኙነትታቸውን ማጠናከር፡፡
ሀገራቱ ከስትራቴጂካዊ ግንኙነቶቻቸው የጋራ ተጠቃሚ ለመሆን እንደሚሠሩ መግባባት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X