የአፍሪካ ኅብረት በሱዳን ለተቋቋመው ትይዩ መንግሥት እውቅና እንዳይሰጥ ጥሪ አቀረበ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአፍሪካ ኅብረት በሱዳን ለተቋቋመው ትይዩ መንግሥት እውቅና እንዳይሰጥ ጥሪ አቀረበ
የአፍሪካ ኅብረት በሱዳን ለተቋቋመው ትይዩ መንግሥት እውቅና እንዳይሰጥ ጥሪ አቀረበ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 30.07.2025
ሰብስክራይብ

የአፍሪካ ኅብረት በሱዳን ለተቋቋመው ትይዩ መንግሥት እውቅና እንዳይሰጥ ጥሪ አቀረበ

የኅብረቱ የሰላምና ደህንነት ምክር ቤት "ሁሉም የአፍሪካ ኅብረት አባል ሀገራት እና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሱዳንን መበታተን እንዲቃወሙ እና በሰላም ጥረቶች እና በሀገሪቱ የወደፊት ኅልውና ላይ ከፍተኛ መዘዝ ላለው 'ትይዩ መንግሥት' ተብዬ እውቅና እንዳይሰጡ ጥሪ አቅርቧል፡፡"

ዓለም አቀፍ እውቅና ያለው የሱዳን መንግሥት ጎረቤት ሀገራት እና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ አማፂ ላቋቋመው መንግሥት እውቅና እንዳይሰጡ ማክሰኞ አሳስቧል፡፡

ℹ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በቁጥጥሩ ስር ባሉ አካባቢዎች የራሱን መንግሥት አዋቅሮ ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሾመ ባሳለፍነው ቅዳሜ አስታውቋል፡፡ ይህ መንግሥት በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል አዛዥ ሞሐመድ ሃምዳን ዳጋሎ የሚመራ ሲሆን የሱዳን ሕዝባዊ የነጻነት ንቅናቄ-ሰሜን መሪ አብዱልአዚዝ አደም አል-ሂሉ ምክትላቸው ሆነው ተሹመዋል፡፡

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0