የአፍሪካ ልማት ባንክ የልማት ፈንድ በሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያዎች ሊሳተፍ መሆኑ አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአፍሪካ ልማት ባንክ የልማት ፈንድ በሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያዎች ሊሳተፍ መሆኑ አስታወቀ
የአፍሪካ ልማት ባንክ የልማት ፈንድ በሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያዎች ሊሳተፍ መሆኑ አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 30.07.2025
ሰብስክራይብ

የአፍሪካ ልማት ባንክ የልማት ፈንድ በሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያዎች ሊሳተፍ መሆኑ አስታወቀ

በየዓመቱ 5 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ለመሰብሰብ ግብ አስቀምጧል፡፡

"በሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያዎች የገንዘብ ድጋፍ የማሰባሰብ መሻት አለን፤ ይህም ራሳችንን የምንደግፍበት አማራጮችን እንድናሰፋ ይረዳናል" ሲሉ የአፍሪካ ልማት ባንክ የሀብት ማሰባሰብ ኃላፊ ቫሌሪ ዳባዲ በጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ ገልፀዋል፡፡

የአሜሪካ የ555 ሚሊነን ዶላር ቅነሳን ጨምሮ የድጋፍ ቅነሳ ያጋጠመው የአፍሪካ ልማት ፈንድ ወደ አዲስ ወሳኝ መንገድ እያቀና ነው፡፡

🟠 የወቅቱ ጂኦፖለቲካዊ ለውጦች በ2027ሊጀመር ወደ ታቀደው የገበያ ብድር ገፊ ሆነዋል፣

🟠 የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያዎች ለመቀላቀል የመመሥረቻ ቻርተሩን እያሻሻለ ነው፣

🟠 የአፍሪካ ልማት ፈንድ የአፍሪካ ልማት ባንክን ሞዴል በመከተል የብድር ደረጃ ለማግኘት እና የፋይናንስ ሰነዶችን ለማውጣት ወጥኗል፡፡

ቀጣዩ የአፍሪካ ልማት ፈንድ የሦስት ዓመት የማጠናከሪያ ምዕራፍ በህዳር ወር ይጀምራል፡፡ የመጀመሪያው ዕቅድ 25 ቢሊየን ዶላር ለመድረስ ቢሆንም፤ የገንዘብ እጥረት በመኖሩ የማይመስል እንደሆነ ዳባዲ አምነዋል፡፡ የመጀመሪያው የገንዘብ ማሰባሰቢያ ምዕራፍ 8.9 ቢሊየን ዶላር አስገኝቷል፡፡

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0