የውጭ ምንዛሪ ፍሰት “በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ” 32 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር መደረሱን ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ
18:00 30.07.2025 (የተሻሻለ: 18:04 30.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየውጭ ምንዛሪ ፍሰት “በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ” 32 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር መደረሱን ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የውጭ ምንዛሪ ፍሰት “በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ” 32 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር መደረሱን ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ
ባንኩ የኢትዮጵያ የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የተተገበረበትን አንደኛ ዓመት አስመልክቶ ባወጣው ሪፖርት፤ በሪፎረሙ የመጀመሪያ ዓመት ብቻ የውጭ ምንዛሪ ፍሰት 33 በመቶ አድጎ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ 32 ቢሊየን ዶላር መድረሱን ገልጿል፡፡
ከዚህ የውጭ ምንዛሪ ፍሰት መጠን መጨመር የተነሳ፦
19 ቢሊየን ዶላር ያህል ለሸቀጦች ገቢ ንግድ፣
6.7 ቢሊየን ዶላር ለአገልግሎት ገቢ ንግድ፣
1.4 ቢሊየን ዶላር ለውጭ እዳ ክፍያ ውሏል፣
የብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ክምችት በሦስት እጥፍ፤ የንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ ሀብት ደግሞ በሁለት እጥፍ አድጓል፡፡
ባንኮች ለንግድ ድርጅቶች በየዕለቱ የሚያቀርቡት አማካይ የውጭ ምንዛሬ መጠን ሪፎርሙ በተጀመረበት ወቀት ከነበረበት 11 ሚሊየን ዶላር በአሁኑ ወቀት ወደ 25 ሚሊየን ከፍ ማለቱን ሪፖርቱ ጠቁሟል፡፡ አምና ለንግድ ድርጅቶች ይቀርብ የነበረው 258 ሚሊየን ዶላር ወርሃዊ የውጭ ምንዛሪ መጠን ዘንድሮ ወደ 500 ሚሊየን ዶላር አድጓል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X