የጋናው ፕሬዝዳንት አካታች አስተዳደር እና የዜጎች መብቶች ጥበቃ ከቃል ይልቅ በተግባር እንዲገለፅ ጠየቁ

ሰብስክራይብ

የጋናው ፕሬዝዳንት አካታች አስተዳደር እና የዜጎች መብቶች ጥበቃ ከቃል ይልቅ በተግባር እንዲገለፅ ጠየቁ

ጆን ድራማኒ ማሐማ፤ እነዚህ ምሰሶዎች ለአፍሪካ መንግሥታት ቅቡልነት ወሳኝ መሆናቸውን በ13ኛው የአፍሪካ ሕብረት የዲሞክራሲ፣ የሰብዓዊ መብቶች እና የአስተዳደር ከፍተኛ የምክክር መደረክ ላይ ተናገረዋል፡፡

"የሲቪክ ምህዳራችንን ለመጠበቅ በሁሉም አባል ሀገራት ላይ አስገዳጅ የሕግ ማዕቀፎች እንዲኖሩ ይህ ምክክር በጽናት እንዲቆም አሳስባለሁ። የወጣቶች፣ የሴቶች እና የተገለሉ ቡድኖች ድምጽ መደመጥ እና መጠበቅ አለበት" ነው ያሉት።

ፕሬዝዳንቱ አክለውም፤ ወጣቶች "ትዕግሥት እያጡ" እንዲሁም በአፍሪካ የወደፊት እጣ ፈንታ "ዕድል እና ድርሻ" እንዲኖራቸው እየጠየቁ በመሆኑ፤ ተጨባጭ እርምጃ ለመውሰድ የአፍሪካ መሪዎች "ከቅንጡ ንግግሮች" ተሻግረው እንዲጓዙ ጠይቀዋል፡፡

“የዲሞክራሲ ተቋማቶቻችን ዜጎቻቸን የሚረዱትን እና የሚያምኑትን ቁንቋ ይናገሩ” ሲሉም አጽንዖት ሰጠተዋል፡፡

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣሕለወርቅ ዘውዴ በምክክሩ ላይ ተሳትፈዋል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0