ብሔራዊ የግብርና ፋይናንስ ትግበራ ፍኖተ ካርታ ይፋ ሆነ
16:59 30.07.2025 (የተሻሻለ: 17:04 30.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ብሔራዊ የግብርና ፋይናንስ ትግበራ ፍኖተ ካርታ ይፋ ሆነ
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክና በግብርና ሚኒስቴር በጋራ የተነደፈው ይህ ውጥን፤ ከሀገሪቱ የኢኮኖሚ ማሻሻያ፣ የአሥር ዓመት የልማት ዕቅድና ብሔራዊ የግብርና ኢንቨስትመንት ዕቅድ ጋር የተጣጣመ ነው።
"ይህ ተነሳሽነት የፋይናንስ ተቋማት በገጠር ትራንስፎርሜሽን ውስጥ እንደ ስትራቴጂካዊ አጋር እንዲሳተፉ መድረክ ይፈጥራል፡፡ እንደ አበዳሪ ብቻ ሳይሆን ሁሉን አቀፍ እድገት ለማስፈንም ይሠራሉ" ሲሉ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ በማስጀመሪያ መርሃ-ግብሩ ላይ ተናግረዋል፡፡
የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ በበኩላቸው የፍኖተ ካርታው ትግበራ በግብርና ሚኒስቴር በበላይነት በሚቆጣጠረው አስተባባሪ ኮሚቴ እና እቅዱን በውጤታማነት ለማስፈጸም በተቋቋመው የቴክኒክ ኮሚቴ ድጋፍ እንደሚመራ አመልክተዋል።
ሀገራዊ ስትራቴጂው አርሶና አርብቶ አደሮች የባንክ አገልግሎትን ለማግኘት የሚያጋጥሟቸውን ከፍተኛ ወጪና የጊዜ መጓተት ለመፍታት ያለመ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
