ኢትዮጵያ ከአምስት ዓመት በኋላ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪዎችን ምገባ ሙሉ ለሙሉ ለማሳካት እየሠራች መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ ከአምስት ዓመት በኋላ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪዎችን ምገባ ሙሉ ለሙሉ ለማሳካት እየሠራች መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ
ኢትዮጵያ ከአምስት ዓመት በኋላ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪዎችን ምገባ ሙሉ ለሙሉ ለማሳካት እየሠራች መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 30.07.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ከአምስት ዓመት በኋላ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪዎችን ምገባ ሙሉ ለሙሉ ለማሳካት እየሠራች መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ

የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፤ ኢትዮጵያ በአፍሪካ በትምህርት ቤት ምገባ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ካደረጉ ሀገራት አንዷ እንደሆነች፤ በሁለተኛው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓት ጉባኤ የትምህርት ቤት ምገባን ከተመለከተ ውይይት በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ ላይ ገልፀዋል፡፡

በትምህርት ቤት ምገባ አማካኝነት የተመጣጠነ ምግብ ለህጻናት ማቅረብ በተባበሩት መንግሥታት የ2030 ዘላቂ የልማት ግቦች ከተቀመጡ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ነው።

ሚኒስትሩ "መንግሥት ለትምህርት ጥራት፣ ለልጆች ጤና፣ ለተመጣጠነ ምግብ እና እኩልነት፤ የተማሪዎች ምገባን እንደ ዋና አጀንዳ በማድረግ ግቡን ለማሳካት ውጤታማ ተግባራትን እያከናወነ ነው" ብለዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሐመድ በበኩላቸው የትምህርት ቤት ምገባ በዘላቂ የልማት ግቦች ትኩረት ከተሰጣቸው ነጥቦች መካካል እንደሆነ አንስተዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0