"እኔ ሥልጣን ላይ እያለሁ ዳግም ግጭትና ጦርነት አይኖርም" - የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት
15:02 30.07.2025 (የተሻሻለ: 15:04 30.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ"እኔ ሥልጣን ላይ እያለሁ ዳግም ግጭትና ጦርነት አይኖርም" - የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
"እኔ ሥልጣን ላይ እያለሁ ዳግም ግጭትና ጦርነት አይኖርም" - የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት
ሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ በመቐለ ከሰላም ልዑክ ጋር ባደረጉት ውይይት "በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሠረት ተፈናቃዮቻች ወደ ቄያቸው ስላልተመለሱ ጅምር ሰላሙ ሙሉ መሆን አልቻለም" ብለዋል።
የክልሉ አስተዳዳሪ "በትግራይ በኩል የሚጀመር ጦርነት አይኖርም፡፡ እኔ በሥልጣን እያለሁኝ የሚነሳ ጦርነት የለም፤ ዳግም ጦርነትና ግጭት እንዳይቀሰቀስ አቅሜን አሟጥጬ እሠራለሁ" ሲሉ በአፅንዖት ተናግረዋል።
"ሁሉም ልዩነቶች በጠረጴዛ ውይይት ዙሪያ ይፈታሉ" ያሉት የሰላም ልዑካኑ፤ ተፈናቃዮቹ በሰላማዊ መንገድ እንዲመለሱ ለሚደረገው ጥረት ድጋፋቸው እንደሚቀጥሉ ቃል መግባታቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
በፌደራል መንግሥት እና በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር መካከል ሰላማዊ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያግዝ የስምምነት ሰነድ በሁለቱም ወገኖች ተቀባይነት አግኝቷልም ተብሏል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X