ሩሲያ ከኒጀር ጋር ያላትን የኢነርጂ እና የወታደራዊ ግንኙነት ያጠናከረችበት ወሳኝ ጉበኝት

ሩሲያ ከኒጀር ጋር ያላትን የኢነርጂ እና የወታደራዊ ግንኙነት ያጠናከረችበት ወሳኝ ጉበኝት
ሃምሌ 21 ሮሳቶም እና የኒጀር የኢነርጂ ሚኒስቴር በሩሲያ የኢነርጂ ሚኒስትር የኒያሜ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ወቅት የሰላማዊ የኒውክሌር የኢነርጂ አግለግሎት የትብብር ስምምነት ተፈራረመዋል፡፡
የሩሲያ የኢነርጂ ሚኒስቴር “የኛ ተልዕኮ በዩራኒየም ቁፋሮ ላይ መሳተፍ ብቻ አይደለም፤ በኒጀር የሰላማዊ የአቶሚክ ኃይል ለማልማት አጠቃላይ ሥርዓቱን መፈጠር አለብን” ብሏል፡፡
ስምምነቱ የኃይል ማመንጫ መሠረተ ልማቶችን መገንባት፣ በኒውክሌር ሕክምና መተባባር እና ባለሙያዎችን ማሠልጠን ያካትታል፡፡
የሩሲያ ልዑካን የኒጀር ጉብኝት ሌሎች ጉዳዮች፦
የሩሲያ ምክትል የመከላከያ ሚኒስትርና የጦር ጄኔራል ዩኑስ-ቤክ ዬቭኩሮቭ እና ሌተናል ጄኔራል አንድሪ አቬሪያኖቭ፤ የወታደራዊ ስልታዊ ትብብሮችን ለማጠናከር ከኒጀር የመከላከያ ሚኒስትር ሳሊፉ ሞዲ ጋር ተገናኝተው መክረዋል፡፡
የሩሲያው ልዑክ ለወዳጅነታቸው ምልክት ይሆን ዘንድ የአምበር ሥዕል ለኒጀር የመከላከያ ሚኒስትር አበርክተዋል፡፡
የኢነርጂ ሚኒስትር ትሲቪሌቭ የኒጀርን መሪ አብዱራሕማኔ ትያኒን አግኝተዋል፡፡
ትሲቪሌቭ የንግድ እና ኢኮኖሚ የበይነ መንግሥታት ኮሚሽን ምሥረታን በተመለከተ ከጠቅላይ ሚኒስትር አሊ ማሃማን ላሚን ዜይን ጋር ተወያይተዋል፡፡
የሩሲያ ልዑካን ከመከላከያ፣ ከኢነርጂ፣ ከፋይናንስ፣ ከኢንዱስትሪ፣ ከትራንስፖርት እና ከትምህርት ሚኒስቴሮች እንዲሁም እንደ ሮሳቶም፣ ስበርባንክ፣ ካምኤዚ፣ ኖርድ ጎልድ፣ ሮስኮስሞስ እና ሮስጂዎሎጂያ የተውጣጡ ናቸው፡፡
ከኒያሜ በኋላ ልዑካኑ የአፍሪካ ጉብኝታቸውን በመቀጠል ወደ ማሊ ያመራሉ፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X


