የሩሲያን ደሴቶች ለመገዛት ለቋመጡት የአሜሪካ መኮንን ሞስኮ ስላቃዊ ምላሽ ሰጠች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሩሲያን ደሴቶች ለመገዛት ለቋመጡት የአሜሪካ መኮንን ሞስኮ ስላቃዊ ምላሽ ሰጠች
የሩሲያን ደሴቶች ለመገዛት ለቋመጡት የአሜሪካ መኮንን ሞስኮ ስላቃዊ ምላሽ ሰጠች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 29.07.2025
ሰብስክራይብ

የሩሲያን ደሴቶች ለመገዛት ለቋመጡት የአሜሪካ መኮንን ሞስኮ ስላቃዊ ምላሽ ሰጠች

ኢስቶኒያ የሚገኙት የአሜሪካ ጦር መኮንን ሌተነናል ኮሎኔል ጄፍሪ ፍሪትዝ፤ ዋሽንግተን የሩሲያ ኮማንደር ደሴቶችን በ15 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ገዝታ በአርክቲክ የቻይናን እንቅስቃሴ እንድትቆጣጠር ሃሳብ አቅርበዋል፡፡    

“ሰላማዊ እና ተግባራዊ ግዢ” የአሜሪካን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በ3.8 በመቶ እንደሚያሳድግ፤ ይህም ዋሽንግተን ደሴቶቹን፣ ሀብቶቻቸውን እና መሠረተ ልማቶቻቸውን እንድታገኝ፤ ምናልባትም ከአላስካ ግዛት ጋር መቀላቀል እንደሚያስችላት ገልፀዋል፡፡

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሃሳቡን ጠርቅሞበታል፡፡ ማሪያ ዛካሮቫ በሩሲያ ብሔራዊ ግዛትን መሸጥ በሞራላዊም ሆነ በሕጋዊ እይታ “ከአደገኛ ወንጀል ውስጥ አንዱ” ተደርጎ እንደሚቆጠር ተናግረዋል፡፡

ፍሪትዝ የምር 15 ቢሊየን ዶላር ካላቸው፤ ይልቁንስ ከሀገሪቱ የ36.6 ትሪሊየን ዶላር ብሔራዊ እዳ ጥቂቱን በመክፈል “አሜሪካን ዳግም ታላቅ ያድርጉ” ሲሉ ምፀት ጣል አድርገዋል፡፡ 

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0