የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ‘ቅቡልነት የሌለው መንግሥት’ ፈራሽ ነው ሲሉ የሱዳን መልዕክተኛ ለስፑትኒክ ተናገሩ

ሰብስክራይብ

የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ‘ቅቡልነት የሌለው መንግሥት’ ፈራሽ ነው ሲሉ የሱዳን መልዕክተኛ ለስፑትኒክ ተናገሩ

ያለ ግዛት ቁጥጥር ወይም የሕዝብ ሥልጣን አማጺው የጦር አንጃ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በዳርፉር ያቋቋመው ‘የአንድነት እና የሰላም መንግሥት’፤ ሕገወጥ ነው ያሉት በሩሲያ የሱዳን አምባሳደር ሞሐመድ ኤልጋዛሊ ኤልቲጋኒ ሲራጅ ናቸው፡፡

አምባሳደር ሲራጅ የአማፂያኑ እንቅስቃሴ የገጠመውን “ከፍተኛ ውግዘት" በመጥቀስ፤ “እኛ በሱዳን ጦር፣ በአጋዥ እንቅስቃሴዎች እና በሱዳን ሕዝብ በሚገኙ ተጨማሪ ድሎች ይህን መንግሥት እንጋፈጠዋለን” ሲሉ ለስፑትኒክ ተናግረዋል፡፡

ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ወረራ ከፈፀመባቸው አካባቢዎች ካልወጣ፣ ትጥቁን ካልፈታ እና የፖለቲካ ምኞቱን ካልጣለ የሰላም ውይይቶች (የጅዳ እና ኢጋድ) እንደማይቀጥሉ አጽንዖት ሰጥተዋል፡፡

ስለ ዓለም አቀፍ አሰላለፎች፦

ሩሲያ ለሱዳን ሉዓላዊነት እና ቅቡልነት ላደረገችው ‘የመርሆ ድጋፍ’ አመስግነዋል፡፡

የአውሮፓ ሕብረት በሱዳን አካላት ላይ የጣለውን ተቀባይነት የሌለው ማዕቀብ በማውገዝ፤ ብራሰልስ ብሔራዊ ሠራዊትን ከአማጺያን ጋር በሀሰት መመዘኑን ከስሰዋል፡፡

ግብጽ የግዛት አንድነት በማስጠበቅ ረገድ ላደረገችው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡

የተባበሩት የአረብ ኤሚሬቶችን በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ወንጀሎች ተሳታፊነት በመክሰስ፤ ለውይይት ያቀረበችውን ጥሪ "እውነተኛ ያልሆነ" እና "የማይገባ" በማለት አጣጥለውታል፡፡

አምባሳደሩ የአፍሪካ ኅብረት የፈጥኖ ደራሽ መንግሥትን አጥብቆ ማውገዙን በአዎንታ ተቀብለው፤ የአማጺ ቡድኑ ድርጊት "ለአፍሪካ መንግሥታት መበትን" አደገኛ ምሳሌ እንደሚሆን አስጠንቅቀዋል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0