በአዲስ አበባ ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱ ተገለፀ
17:46 29.07.2025 (የተሻሻለ: 17:54 29.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበአዲስ አበባ ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱ ተገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በአዲስ አበባ ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱ ተገለፀ
በአዲስ አበባ በዓመት ከመነጨው 100 ሺህ 585 ቶን፤ ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል ከ1.69 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ወንድሙ ሴታ ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ገልፀዋል። በከተማዋ 325 የመልሶ መጠቀም ማኅበራት አሉ፡፡
በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት፦
983 ሺህ 944 ቶን ቆሻሻ ተመርቷል፣
5 ሺህ 460 ቶን ቆሻሻን ወደ ኮምፖስት በመቀየር ለከተማዋ የአረንጓዴ ልማት ሥራ ውሏል፣
675 ሺህ 384 ነዋሪዎች እና 2 ሺህ 540 ተቋማት በሳምንታዊ የጽዳት ዘመቻ ተሳትፈዋል::
በአጠቃላይ በተሠራው የጽዳት ሥራ በከተማዋ የሚከሰቱ የወረርሽኝ ምጣኔዎችን መቀነስ፣ ወንዟችና አካባቢን ከብክለት መታደግ፣ ቆሻሻን ወደ ሀብት መቀየር እና ከተማዋን ውብና ጽዱ ማድረግ ተችሏል ተብሏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X