በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር 8.5 ቢሊዮን የቡና ችግኞች ተተክለዋል - ግብርና ሚኒስቴር
16:57 29.07.2025 (የተሻሻለ: 17:04 29.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር 8.5 ቢሊዮን የቡና ችግኞች ተተክለዋል - ግብርና ሚኒስቴር
የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የቡና ገበያ ላይ ያላትን ድርሻ ለማስጠበቅ ጥራት ያለው ቡናን በስፋት የማምረት ሥራ እየሠራች እንደምትገኝ፤ የአፍሪካን የቡና እሴት ሰንሰለት ሽግግር ማሳደግ ያለመ የምክክር መድረክ ላይ ተናገረዋል፡፡
ሚኒስትሩ የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ ኢትዮጵያ እያከናወነቻቸው የሚገኙ ተግባራትን ዘርዝረዋል፦
🟤 በስድስት ዓመታት የቡና ምርታማነት ከ500 ሺህ ወደ 1.2 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን አድጓል፣
🟤 በእዚህ ዓመት ቡናን ለውጭ ገበያ በማቅረብ 2.6 ቢሊየን ዶላር ተገኝቷል፣
🟤 የሄክታር ምርታማነትም ከ0.6 ሜትሪክ ቶን ወደ 0.9 ሜትሪክ ቶን ከፍ ብሏል፣
🟤 ለውጭ ገበያ የሚቀርብ የቡና መጠንም ከ469 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ድርሷል፣
🟤 ከ2 ሺህ በላይ ቡና አምራች የኢትዮጵያ ገበሬዎች ዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ቀጥተኛ ንግድ እያከናወኑ ነው፡፡
ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ ኢትዮጵያ ቡናን ለውጭ ገበያ በማቅረብ ከአፍሪካ መሪ መሆኗንም እንደገለፁ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X