ታይላንድ እና ካምቦዲያ ተኩስ ለማቆምና በጋራ ድንበራቸው ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ለመግታት ተስማሙ
17:03 29.07.2025 (የተሻሻለ: 17:04 29.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ታይላንድ እና ካምቦዲያ ተኩስ ለማቆምና በጋራ ድንበራቸው ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ለመግታት ተስማሙ
በአወዛጋቢው የድንበር አካባቢ የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ በማለም በሁለቱ ሀገራት ባለሥልጣናት የሁለት ዙር ስብሰባ ከተደረገ በኋላ የመጣ ውሳኔ መሆኑን ባንግኮክ ፖስት ዘግቧል፡፡
የድንገተኛ ጊዜ መገናኛዎች እንደሚመሠረቱም ተዘግቧል፡፡
ይህ የተኩስ አቁም ስምምነት ቢያንስ የሁለቱ ሀገራት የመከላከያ ሚኒስትሮች በካምቦዲያ መዲና ፐኖም ፔን ለመገናኘት ቀጠሮ አስከያዙበት ነሃሴ 4 ድረስ ሊቆይ እንደሚችል ይጠበቃል፡፡
በተመሳሳይ የታይላንድ እና የካምቦዲያ ጦሮች ትናንት በተፈረመው የተኩስ አቁም ስምምነት ትግበራ ዙሪያ ድርድር ጀምረዋል፡፡
እነዚህ ውይይቶች እንደተጠበቁ ሆነው፤ ድንበር አካባቢ ግጭቶች መቀጠላቸው እየተዘገበ ነው፡፡ ታይላንድ ካምቦዲያን የተኩስ አቁሙን በመጣስ ስትከስስ፤ ፐኖም ፔን ግን አስተባብላለች፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X