የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያ ለአቮካዶ ምርት የሰጠችውን ትኩረት እና በዘርፉ እያስመዘገበች ያለውን ስኬት አደነቁ
15:04 29.07.2025 (የተሻሻለ: 16:44 29.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየናይጄሪያ ምክትል ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያ ለአቮካዶ ምርት የሰጠችውን ትኩረት እና በዘርፉ እያስመዘገበች ያለውን ስኬት አደነቁ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያ ለአቮካዶ ምርት የሰጠችውን ትኩረት እና በዘርፉ እያስመዘገበች ያለውን ስኬት አደነቁ
መሰል ተግባራት በአህጉር ደረጃ መበረታታት እንደሚገባቸውም አሳስበዋል።
ሶስተኛ ቀኑን ከያዘው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ስርዓት ጉባኤ ጎን ለጎን “የመጪው ትውልድ የግብርና ምግብ ሥራ ፈጣሪዎች እና የአፍሪካ ወጣት መሪዎች የጋራ የምክክር መድረክ” እንደተካሄደ በቦታው የሚገኘው የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል።
በዚሁ ወቅት የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዝዳንት ካሺም ሸቲማ ለወጣት አፍሪካውያን ባስተላለፉት መልዕክት “መጪው ጊዜ የናንተ ነው። የአየር ንብረት ለውጥንም ሆነ መሰል ተግዳሮቶችን በመቋቋም አስተማማኝ የግብርና የሥራ ፈጠራ ስርዓትን እውን እንደምታደርጉ አምናለሁ” ብለዋል።
የግብርና ሥራ ፈጠራ አቅምን ለማዳበር መሪዎች ለዘላቂ የአካባቢ ጥበቃ፣ ለፋይናንስ እና ለኃይል አቅርቦት ያላሰለሰ ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባም ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
