የሩሲያ እና አፍሪካ ታሪካዊ መሠረት ያለው ግንኙነት መጠናከር አለበት - ባለሙያ
12:14 29.07.2025 (የተሻሻለ: 13:34 29.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሩሲያ እና አፍሪካ ታሪካዊ መሠረት ያለው ግንኙነት መጠናከር አለበት - ባለሙያ
ኮትዲቯራዊው ምሁር አዱ ያኦ ናይኬዝ፤ ሩሲያ በአፍሪካ የቅዥ ግዛት ታሪክ የሌላት በመሆኑ ትከበራለች፤ ሆኖም በጅምር ላይ ያሉ ጥረቶች ለወጣቱ ትውልድ አስፈላጊ የሆኑ ታሪካዊ አሻራዎችን ማስቀጠል አለባቸው ሲሉ በፕሪቶሪያው ሦስተኛ የቫልዳይ ሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ ተናግረዋል፡፡
ናይኬዝ ትምህርታዊ መርሃ-ግብሮችን በማጉላት፤ በአሁኑ ወቀት በሩሲያ ትምህርት እየተከታተሉ የሚገኙ ወደ 30 ሺህ ገደማ አፍሪካውያን ተማሪዎች ታሪካዊውን የአፍሪካ እና ሩሲያ የሁለትዮሽ ግንኙነት ለመጠበቅ ቁልፍ ናቸው ብለዋል፡፡
የደቡብ አፍሪካ የትብብር ጽሕፈት ቤት መሪ ልዋዚ ሶሚያ በበኩላቸው ሩሲያ በአፍሪካ ያላት "ሶፍት ፓወር" ጥሩ የሚባል ቢሆንም፦
🟠 ቀጣይነት ያለው ድጋፍና ዕድገት እንደሚያስፈልገው፣
🟠 በአኅጉሪቱ የሶቪዬት ሕብረትን አሻራ፣ በቅኝ ግዛት መፍረስ እና በሀገረ መንግሥት ግንባታ ላይ የነበራትን አበርክቶ መርሳት እንዳለ አንስተዋል፡፡
ሁለቱ ባለሙያዎች ታሪካዊ ትውስታን ጠብቆ ማቆየት ዲፕሎማሲን፣ የዓለም አቀፍ ተቋማትን እና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን ጨምሮ በሁሉም ደረጃዎች ተሳትፎን እንደሚጠይቅ ተስማምተዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X