እሴትን ከማውጣት ወደ መገንባት፦ የደቡብ አፍሪካ የፖሊሲ ምርምር ማዕከል ኃላፊ በተለዋዋጭ ዓለም አቀፍ ሥርዓት ውስጥ የአፍሪካን ራዕይ አስረድተዋል
እሴትን ከማውጣት ወደ መገንባት፦ የደቡብ አፍሪካ የፖሊሲ ምርምር ማዕከል ኃላፊ በተለዋዋጭ ዓለም አቀፍ ሥርዓት ውስጥ የአፍሪካን ራዕይ አስረድተዋል
የግሎባል ዲያሎግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ፊላኒ ምተምቡ፤ አፍሪካ ቀጣናዊ የእሴት ሰንሰለቶችን በመፍጠር በስትራቴጂካዊ መንገድ ኢንዱስትሪዎችን መገንባት አለባት ሲሉ በፕሪቶሪያ ከተካሄደው ሦስተኛው የቫልዳይ ሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ጎን ለጎን ተናግረዋል፡፡
የአየር ንብረት የገንዘብ ድጋፍ፣ የእዳ ቅነሳ እና በተለይም ከአሜሪካ ዶላር ጥገኝነት ያልወጣውን የዓለም አቀፍ የብድር ሥርዓት የማሻሻል አስፈላጊነትን አጉልተዋል፡፡
የሩሲያ-አፍሪካ የግብርና ትብብር እንዲጠናከር አጽዕኖት በመስጠት፤ “ሩሲያ ወታደራዊ ኃይል ብቻ ሳትሆን የግብርናም ኃይል ናት” ሲሉ ምተምቡ ለስፑትኒክ ተናገረዋል፡፡
ሰለደቡብ አፍሪካ የቡድን 20 ፕሬዝዳንትነት ሲያብራሩ፤ ሀገሪቱ እንደ የኢንዱስትሪ ዕድገት፣ ወሳኝ ማዕድናት እና እዳ ማሻሻያ ያሉ ቁልፍ የደቡባዊውን ዓለም ትኩረቶች እንድታነሳ እድል የሚፈጥርላት መሆኑን ጠቁሟል፡፡
በመጨረሻም ዶ/ር ምተምቡ የብሪክስ ምሥረታ ዓላማ እንዳይዘነጋ በማስጠንቀቅ ፤ በተለይም የምዕራባውያን ማዕቀቦች እየጨመሩ በመጡበት በአሁኑ ወቅት የሀገር ውስጥና ቀጣናዊ የክፍያ ሥርዓቶች እንዲጠናከሩ ጠይቀዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X