በሞሪታኒያ የባሕር ዳርቻ የጀልባ ሞተር ብልሽት የገጠማቸው በደርዘን የሚቆጠሩ ምዕራብ አፍሪካዊያን ስደተኞችን ሕይወት ማትረፍ ተቻለ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበሞሪታኒያ የባሕር ዳርቻ የጀልባ ሞተር ብልሽት የገጠማቸው በደርዘን የሚቆጠሩ ምዕራብ አፍሪካዊያን ስደተኞችን ሕይወት ማትረፍ ተቻለ
በሞሪታኒያ የባሕር ዳርቻ የጀልባ ሞተር ብልሽት የገጠማቸው በደርዘን የሚቆጠሩ ምዕራብ አፍሪካዊያን ስደተኞችን ሕይወት ማትረፍ ተቻለ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 28.07.2025
ሰብስክራይብ

በሞሪታኒያ የባሕር ዳርቻ የጀልባ ሞተር ብልሽት የገጠማቸው በደርዘን የሚቆጠሩ ምዕራብ አፍሪካዊያን ስደተኞችን ሕይወት ማትረፍ ተቻለ

ሐምሌ 15 ቀን ከጊኒ የባሕር ዳርቻ ከተማ ካምሳር የተነሳችው ጀልባ፤ የአደጋ ጥሪ ከመደረጉ በፊት ልትሰጥም ተቃርባ እንደነበር ተገልጿል። ስደተኞቹ የጀልባ ሞተር ከተበላሸ በኋላ ለሁለት ቀናት ያህል መስመር ስተው ባሕሩ ላይ ተንሳፍፈው ቆይተዋል።

ባለሥልጣናት እንደገለጹት ጀልባዋ ጊኒን፣ ሴኔጋልን እና ጋምቢያን ጨምሮ ከተለያዩ ምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ቢያንስ 75 ስደተኞችን ይዛ ነበር። በአቅራቢያ የነበረች ጀልባ ስደተኞቹን የሞሪቴኒያ የባሕር ጠረፍ ጥበቃ ከመረከቡ በፊት ድጋፍ አድርጋለች።

በቅርብ ዓመታት ከሰሜን አፍሪካ ተነስተው በባሕር ወደ ስፔን እና ሌሎች የአውሮፓ ሀገራት ለመድረስ የሚሞክሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞት ሕይወታቸው አልፏል።

የስፔን በጎ አድራጎት ድርጅት ካሚናንዶ ፍሮንቴራስ እንዳለው፤ በ2024 ብቻ ወደ ስፔን ለመድረስ የሞከሩ ወደ 10 ሺህ 500 የሚጠጉ ሰዎች በባሕር ላይ ሞተዋል። ይሁን እንጂ ወደ ስፔን ካናሪ ደሴቶች የሚደርሱ ሰዎች ቁጥር ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ቀንሷል።

በእንግሊዘኛ ለማንበብ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0