ፕሬዝዳንት ፑቲን ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር የስልክ ውይይት እንዳደረጉ ክሬምሊን አስታወቀ
18:33 28.07.2025 (የተሻሻለ: 19:04 28.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱፕሬዝዳንት ፑቲን ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር የስልክ ውይይት እንዳደረጉ ክሬምሊን አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ፕሬዝዳንት ፑቲን ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር የስልክ ውይይት እንዳደረጉ ክሬምሊን አስታወቀ
የሩሲያ ወገን በመካከለኛው ምሥራቅ ቀጣና ያሉ ችግሮችን እና ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ እልባት ለመሰጠት ያለውን ጽኑ አቋም አረጋግጧል።
ፑቲን የሚከተሉትን ጉዳዮች አስፈላጊነት አጽንዖት ሰጥተዋል፦
🟠 የሶሪያን አንድነት፣ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት መደገፍ፣
🟠 የሁሉንም የጎሳ እና የሐይማኖት ቡድኖች ሕጋዊ መብቶች እና ጥቅሞች በማክበር የሶሪያን የውስጥ ፖለቲካዊ መረጋጋት ማጠናከር፣
የሰሞኑ የኢራን እና የእስራኤል ፍጥጫ ግምት ውስጥ በማስገባት፤ የኢራንን የኒውክሌር መርሃ-ግብር በተመለከተ ድርድር ላይ የተመሠረተ መፍትሔ ለማግኘት የሚቻለውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን የሩሲያ ወገን ገልጿል።
መሪዎቹ በዓለም አቀፋዊ እና በሁለትዮሽ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይታቸውን ለማስቀጠል ተስማምተዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X