ሞሮኮ ከአሥር ዓመት ባነሰ ጌዜ ውስጥ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪዋን በከፍተኛ ደረጃ ለውጣለች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሞሮኮ ከአሥር ዓመት ባነሰ ጌዜ ውስጥ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪዋን በከፍተኛ ደረጃ ለውጣለች
ሞሮኮ ከአሥር ዓመት ባነሰ ጌዜ ውስጥ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪዋን በከፍተኛ ደረጃ ለውጣለች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 28.07.2025
ሰብስክራይብ

ሞሮኮ ከአሥር ዓመት ባነሰ ጌዜ ውስጥ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪዋን በከፍተኛ ደረጃ ለውጣለች

ሀገሪቱ በግዝፉ የኢንዱስትሪ ስትራቴጂዋ በማግረብ ቀጣና እና ከዚያም ባሻገር በአውሮፕላን ጥናት ዘርፍ (ኤሮኖቲካል) ዋና ማዕከል እየሆነች ነው።

ቁልፍ አኃዛዊ መረጃዎች፦

የአውሮፕላን እቃዎች የወጪ ንግድ፦ በ2014 ከነበረው 3.73 ቢሊየን ድርሃም (412.9 ሚሊየን ዶላር )፤ በ2024 ወደ 17.2 ቢሊየን ድርሃም ወይም 1.9 ቢሊየን ዶላር በማሳደግ የ460 በመቶ ጭማሪ አግኝታለች፡፡

አጠቃላይ የዘርፉ ዓለም አቀፍ ሽያጭ፦ ከ7.69 ቢሊየን ድርሃም (851.28 ሚሊየን ዶላር) ወደ 26.44 ቢሊየን (2.92 ቢሊየን ዶላር) በማሻቀብ የ244 በመቶ (በአማካይ በየዓመቱ የ13 በመቶ) ጭማሪ አሳይቷል፡፡

የስኬቶቿ ቁልፎች፦

ሥልጠና፦ የሞሮኮ የኤሮኖቲካል ሙያዎች ተቋም፤ እንደ ቦይንግ ያሉ ግዙፍ ኩባንያዎችን የሚስብ ዓለም አቀፍ የሰው ኃይል ያሰለጥናል።

መሠረተ ልማት፦ ለአውሮፓ ያለው ቅርበት፣ ተወዳዳሪ ዋጋዎች፣ ነፃ የንግድ ስምምነቶች እና የፖለቲካ መረጋጋት።

የአካባቢ ሥነ-ምህዳር፦ የንዑስ ተቋራጮች ትሥሥር የኢንዱስትሪ ውህደትን ያጠናክራል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0