የታንዛኒያ የምርጫ ኮሚሽን 8 ሚሊየን አዳዲስ መራጮችን በመመዝገበ ካስቀመጠው ግብ ተሻገረ
17:18 28.07.2025 (የተሻሻለ: 17:24 28.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የታንዛኒያ የምርጫ ኮሚሽን 8 ሚሊየን አዳዲስ መራጮችን በመመዝገበ ካስቀመጠው ግብ ተሻገረ
የአዲስ መራጮች ምዝገባ ከግምቱ በ136.79 በመቶ ብልጫ ማሳየቱን የገለልተኛ ብሔራዊ ምርጫ ኮሚሽን ሊቀ ምንበር ጃኮብስ ምዋምቤጌሌ ተናግረዋል፡፡ ኮሚሽኑ በመጀመሪያ 5.58 ሚሊየን አዳዲስ መራጮችን ለመመዝገብ አቅዶ የነበረ ሲሆን ይህም የ2019/2020 የመራጮች ምዝገባ 18.77 በመቶን ይወክላል፡፡
ምዋምቤጌሌ 4.29 ሚሊየን ነባር መራጮች የምዘገባ መረጃዎቻቸውን ማደሳቸውን ገልጸዋል፡፡ ይህም ከ4.36 ሚሊየን ግብ 98.23 በመቶ የሚወክል ሲሆን ቀደም ሲል ከተመዘገቡ መራጮች 15% በመቶ ገደማ ነው።
ከአዳዲስ ምዝገባዎች እና የመረጃ እድሳቶች በተጨማሪ ኮሚሽኑ ወደ 100 ሺህ የሚጠጉ ብቁ ያልሆኑ ተመዝጋቢዎችን ከመራጮች መዝገብ አስወግዷል፡፡ ምዋምቤጌሌ በተደጋጋሚ የተመዘገቡ ወደ 9 ሺህ የሚጠጉ ግለሰቦች መታወቃቸውን እና ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ተናግረዋል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X