የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት በጋዛ ፍልስጤማውያን ላይ እየተፈፀመ ያለውን 'ሆን ብሎ ማስራብ' አወገዙ

የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት በጋዛ ፍልስጤማውያን ላይ እየተፈፀመ ያለውን 'ሆን ብሎ ማስራብ' አወገዙ
ሲሪል ራማፎሳ በጋውቴንግ በተካሄደው የነጻነት ንቅናቄዎች ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር “በእስራኤል አፓርታይድ መንግሥት በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን እና የዘር ማጥፋት ወንጀል” በማውገዝ፤ በሰላማዊ ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው የቦምብ ጥቃት በአስቸኳይ እንዲቆም ጠይቀዋል።
እስራኤል ያልተገደበ መግቢያ እና አስፈላጊ የሆኑ ዕርዳታዎችን በተለይም ምግብ እንዲከፋፈል እንድትፈቅድ አሳስበው፤ የሕፃናት እና ታዳጊዎችን ከረሃብ ሞት ለመታደግ ዓለም አቀፍ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ አቅርበዋል።
ራማፎሳ በተጨማሪም የፀረ-ቅኝ አገዛዝ ትግልን እና የኢኮኖሚያዊ ፍትሕን አስፈላጊነት በሰፊው በመዳሰስ፤ የነጻነት ንቅናቄዎች “አዲሱን የአፍሪካ ቅርምት” እንዲዋጉ አሳስበዋል።
በተራማጅ ፖሊሲዎች እና በባለብዙ ወገን ላይ የሚፈፀመውን “አዲስ ጥቃት” በማንሳትም፤ አኅጉሪቱን በግብይት ዲፕሎማሲ እና በኢኮኖሚ ማስገደድ ሆን ተብሎ ለመከፋፈል እና ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት አስጠንቅቀዋል።
"አሁን የግዛት ቅርምት አይደለም። ይህ የዲጂታል፣ የኢኮኖሚ፣ የርዕዮተ ዓለም እና ሥነ-ምህዳራዊ ቅርምት ነው" ሲሉ ለአፍሪካ መሪዎች ተናግረዋል።
ራማፎሳ አፍሪካ ለአየር ንብረት ለውጥ አነስተኛ አስተዋፅዖ ብታደርግም፤ ሰሜናዊው ዓለም በአካባቢያዊ ምህዳር ላይ ባደረሰው ብዝበዛ ምክንያት ገፈቱን እየተሸከመች እንደምተገኝ ጠቁመዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X