የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ በበጀት ዓመቱ ከ108 ቢሊየን ብር ማስገባቱን አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ በበጀት ዓመቱ ከ108 ቢሊየን ብር ማስገባቱን አስታወቀ
የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ በበጀት ዓመቱ ከ108 ቢሊየን ብር ማስገባቱን አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 28.07.2025
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ በበጀት ዓመቱ ከ108 ቢሊየን ብር ማስገባቱን አስታወቀ

ይህም ከ2017የበጀት ዓመት የድርጅቱ እቅድ በ107 በመቶ ብልጫ ያለው መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በሪሶ አመሎ እንደተናገሩት "ማክሮ ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያዎች የሎጂስቲክስ ዘርፍ አፈጻጸምን በማሻሻል ረገድ ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል።"

ድርጅቱ በበጀት ዓመቱ፦

የራሱን እና የኪራይ መርከቦችን በመጠቀም 3 ሚሊየን 749ሺ 965 ቶን ገቢ ጭነት፣

40ሺ 999 ወጪ ጭነት በራሱ መርከቦች፣

108ሺ 435 ሃያ ጫማ ኮንቴይነሮችን በመልቲሞዳል የትራንስፖርት ስርዓት ወደ ሀገር ውስጥ ደረቅ ወደቦችና የጉምሩክ ፈቃድ ያላቸው መጋዘኖች አጓጉዟል፡፡

የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ፣ በመጪዎቹ ዓመታት በቅርቡ የሚረከባቸውን 62 ሺህ ቶን የሚጨኑ ሁለት አልትራማክስ ደረቅ የጅምላ ጭነት መርከቦችን ጨምሮ፣ ስድስት አዳዲስ መርከቦችን በመጨመር የጭነት መጓጓዣ መርከቦችን ቁጥር ያሳደጋል። በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ 10 መርከቦች እንዳሏት ይነገራል፡፡

ድርጅቱ በሥራ ላይ በደረሰ ኪሳራ ምክንያት ባሕር ዳር እና ሐዋሳ የተሰኙ መረከቦችን ሸጦ ዓባይ ብሎ የሰየመውን አዲስ መረከብ ከቻይና እንደገዛ ከዚህ በፊት አስታውቋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0