ከታላቁ የሕዳሴ ግድብ ቀጥሎ ሁለተኛው ትልቁ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ ወደ ፍጻሜው አጋማሽ እየተጠጋ ነው ተባለ
12:44 28.07.2025 (የተሻሻለ: 16:04 28.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱከታላቁ የሕዳሴ ግድብ ቀጥሎ ሁለተኛው ትልቁ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ ወደ ፍጻሜው አጋማሽ እየተጠጋ ነው ተባለ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ከታላቁ የሕዳሴ ግድብ ቀጥሎ ሁለተኛው ትልቁ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ ወደ ፍጻሜው አጋማሽ እየተጠጋ ነው ተባለ
ጊቤ ቁጥር 1፣ 2 እና 3 ግድቦችን በሚያስተሳስረው ኦሞ ወንዝ ላይ እየተገነባ ያለው የኮይሻ ግድብ 2.5 ቢሊየን ዩሮ እንደሚፈጅ ተነግሯል፡፡
የኮይሻ ግድብ ዝርዝር መረጃዎች፦
የግድቡ ከፍታ 201 ሜትር ሲሆን 1012 ርዝመት አለው፣
የግድቡ የጎን ስፋት ወደ 1 ኪሎ ሜትር ይጠጋል፣
ግድቡ ሲጠናቀቅ እስከ 130 ኪ.ሜ ርዝማኔ ያለው ሐይቅ ይፈጥራል፣
ከጊቤ 3 ግድብ ጋር የሚገጥም ይሆናል፣
በቀጣይ 3 ዓመታት ሲጠናቀቅ 1 ሺህ 800 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል፡፡
በሳሊኒ ኮንስትራክሽን ኩባንያ እየተገነባ የሚገኘው ኮይሻ ግድብ ሲጠናቀቅ፣ የግብፁን አስዋን ግድብ በመብለጥ ሕዳሴን ተከትሎ ትልቁ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ይሆናል ተብሎ እንደሚጠበቅ፤ በደቡብ ሱዳን የቀድሞው የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል መኽዲ በማህበራዊ ገፃቸው ያጋሩት መረጃ አመልክቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X