ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የራሱ የሆነ የቱሪዝም ብራንድ እንዲኖረው ጥናት እየተደረገ ነው - ቱሪዝም ሚኒስቴር
11:51 28.07.2025 (የተሻሻለ: 11:54 28.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱታላቁ የሕዳሴ ግድብ የራሱ የሆነ የቱሪዝም ብራንድ እንዲኖረው ጥናት እየተደረገ ነው - ቱሪዝም ሚኒስቴር

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የራሱ የሆነ የቱሪዝም ብራንድ እንዲኖረው ጥናት እየተደረገ ነው - ቱሪዝም ሚኒስቴር
በግድቡ ሥፍራ የሚገኘው የጥናት ቡድን የጥናቱን ውጤት በቅርቡ ይፋ እንደሚያደረግ ተገለጿል፡፡
የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ እንደገና አበበ ለሀገር ውስጥ ጋዜጣ እንደገለጹት፤ የቱሪዝም ሚኒስቴር “የዓባይ ግድብ ምን ዓይነት የቱሪዝም ተዝናኖትን ሊፈጥር ይችላል?” በሚል ውሃው እና መልክዓ ምድሩ በቅንጅት በሚፈጥሩት የቱሪዝም መስኅብ የራሱ የሆነ የቱሪዝም ብራንድ እንዲኖረው እየተሠራ ነው፡፡
ግድቡ ከሚሰጠው ከፍተኛ የዓሣ ምርት ባሻገር ያሉት የቱሪዝም ዕድሎች፦
◾ ግድቡ የሚያርፍበት ቦታ የውሃውን ይዞታ ጨምሮ 1 ሺህ 740 ስኩዌር ኪሎ ሜትር መሸፈኑ፣
◾ ግድቡ የሚይዘው 74 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ውሃ ወደ ኋላ 246 ኪሎ ሜትር መርዘሙ፣
◾ እያንዳንዳቸው ከአምስት ሔክታር በላይ ስፋት ያላቸው 70 ደሴቶች መፈጠራቸው፣
◾ 2 ሺህ 800 ሔክታር ስፋት የሚኖረው አንድ ትልቅ ደሴት፡፡
ግድቡን ወደ ዋነኛ የቱሪስት መስኅብነት ለመቀየርም በትኩረት እየተሠራ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ የዓባይ ግድብ የቱሪዝም ዘርፉን የሚያነቃቃ ልዩ ስጦታ መሆኑን ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X