ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአየር ንብረት ለውጥ ፋይናንስ ከምግብ ሥርዓት ጋር እንዲጣጣም ጥሪ አቀረቡ

ሰብስክራይብ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአየር ንብረት ለውጥ ፋይናንስ ከምግብ ሥርዓት ጋር እንዲጣጣም ጥሪ አቀረቡ

2ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብ ስርዓት ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡ መክፈቻው ላይ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ ለልማት የሚደረጉ ድጋፎች በመቀዛቀዛቸው ምክንያት አፍሪካ ጫና ውስጥ እንደምትገኝ እና የባለብዙ ወገን ግንኙነቶች ፈተና እንደገጠማቸውም ገልፀዋል፡፡

አክለውም አፍሪካ በግብርና፣ የገጠር ልማት፣ መሠረተ ልማት እና ቢዝነስ ላይ ኢንቨስት እንድታደርግ ተገማች ፋይናንስ ያስፈልጋታል ብለዋል፡፡

"ከእኛ አውድ ጋር የሚስማሙ ከአየር ንብረት ጋር የተዛመኑ መሳሪያዎች፣ ባዮቴክኖሎጂ እና የዲጂታል ግብርና ያስፈልጉናል። ቴክኖሎጂዎች ተመጣጣኝ እና የጋራ ሊሆኑ እንጂ ሊደበቁ አይገባም” ሲሉ አጽዕኖት ሰጥተዋል።

በኢትዮጵያ እና በጣሊያን ትብብር የሚካሄደው የመሪዎች ጉባኤ ቀጣይነት ያለው፣ አካታች እና የማይበገር የምግብ ስርዓት ግንባታ ላይ አተኩሮ ከሐምሌ 20 እስከ 22 ድረስ ይካሄዳል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአየር ንብረት ለውጥ ፋይናንስ ከምግብ ሥርዓት ጋር እንዲጣጣም ጥሪ አቀረቡ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአየር ንብረት ለውጥ ፋይናንስ ከምግብ ሥርዓት ጋር እንዲጣጣም ጥሪ አቀረቡ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 28.07.2025
አዳዲስ ዜናዎች
0