ኢትዮጵያ በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ከግብፅ ጋር ጦርነት ውስጥ ልትገባ ትችላለች መባሉን ውድቅ አደረገች
19:09 27.07.2025 (የተሻሻለ: 19:44 27.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ከግብፅ ጋር ጦርነት ውስጥ ልትገባ ትችላለች መባሉን ውድቅ አደረገች

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ከግብፅ ጋር ጦርነት ውስጥ ልትገባ ትችላለች መባሉን ውድቅ አደረገች
በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው 6ኛው የፓን አፍሪካ ፓርላማ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያን የወከለው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፓን አፍሪካ ቡድን፤ የግጭት መከላከል ቅድመ ማስጠንቀቂያ የአቻ ግምገማ ላይ በአንድ ጽሑፍ አቅራቢ ለተነሳው ሐሳብ የሰጠው ምላሽ ነው።
ኢትዮጵያ እና ግብፅ ድንበር እንደማይጋሩ የሞገቱት የልዑኩ አባል አወቀ አምዛዬ (ዶ/ር)፤ በሁለቱ ሀገራት መካከል ምንም ዓይነት የድንበር ግጭት እንደሌለ እና ግድቡም የግጭት ምንጭ ሊሆን እንደማይችል አበክረው ገልጸዋል።
"ግጭት እንዲፈጠር ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉት ኢትዮጵያን አግልሎ የአባይን ውሃ የመጠቀም ሙሉ መብት ግብፅ እንድትጎናፀፍ የሚያደርጉ በብሪታንያ፣ ግብፅ እና ሱዳን መካከል የተደረጉ ጊዜ ያለፈባቸው የቅኝ ግዛት ዘመን ስምምነቶች ናቸው" ብለዋል።የአፍሪካ ኅብረት እና የፓን አፍሪካ ፓርላማ እነኚህ የቅኝ ግዛት ስምምነቶች ሙሉ በሙሉ እንዲሰረዙ ብርቱ ጥረት ማድረግ እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X