የኤም23 አማፂያን በእስረኞች ጉዳይ ምክንያት ከኮንጎ ዲሞክራሲያ ሪፐብሊክ ጋር የተደረሠውን የሰላም ስምምነት እንደሚያቋርጡ አስጠነቀቁ
18:46 27.07.2025 (የተሻሻለ: 18:54 27.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኤም23 አማፂያን በእስረኞች ጉዳይ ምክንያት ከኮንጎ ዲሞክራሲያ ሪፐብሊክ ጋር የተደረሠውን የሰላም ስምምነት እንደሚያቋርጡ አስጠነቀቁ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኤም23 አማፂያን በእስረኞች ጉዳይ ምክንያት ከኮንጎ ዲሞክራሲያ ሪፐብሊክ ጋር የተደረሠውን የሰላም ስምምነት እንደሚያቋርጡ አስጠነቀቁ
በምስራቃዊ ኮንጎ ሰፊ ግዛቶችን የተቆጣጠረው ታጣቂ ቡድን በዚህ ወር የተፈረመው "የዶሃ የመርሆች መግለጫ” ቁልፍ አንቀጽ የሆነውን እስረኞችን መፍታት በተመለከተ በኪንሻሳ እየታየ ያለውን መዘግየት አውግዟል።
በዶሃ ነሐሴ ሁለት ቀን ሊካሄድ የታቀደው ድርድር ዳግም ከመጀመሩ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ፤ የኤም23 ቋሚ ጸሃፊ ቤንጃሚን ምቦኒምፓ ጠንካራ መልዕክት አስተላልፏል።
"እስረኞቻችን ካልተፈቱ በዶሃ ምን እንሠራለን? መግለጫው ይህ አንቀጽ ወደ ቀጣዩ ደረጃ ከመሄዳችን በፊት መከበር እንዳለበት ይደነግጋል።"
በኳታር ሽምግልና የተደረሠው የመርህ ስምምነት አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲተገበር ያስቀምጣል። ሆኖም ሁለቱም ወገኖች ስምምነቱን በመጣስ በመወነጃጀላቸው የተኩስ አቁሙን እድሜ አሳጥረዋል።
ℹ ግጭቱ በሰሜንና በደቡብ ኪቩ ግዛቶች እየተጠናከረ ሲሆን የኤም23 አማፅያን ከኮንጎ ጦር ጋር ከተሰለፈው ከዋዛሌንዶ የመከላከያ ቡድን ጋር እየተፋለሙ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X