አልጄሪያ የፈረንሳይ ዲፕሎማቶችን የአውሮፕላን ማረፊያ እና የወደብ ልዩ መብቶች ሰረዘች፤ በሀገራቱ መካከል ያለው አይሏል
16:52 27.07.2025 (የተሻሻለ: 16:54 27.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአልጄሪያ የፈረንሳይ ዲፕሎማቶችን የአውሮፕላን ማረፊያ እና የወደብ ልዩ መብቶች ሰረዘች፤ በሀገራቱ መካከል ያለው አይሏል

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አልጄሪያ የፈረንሳይ ዲፕሎማቶችን የአውሮፕላን ማረፊያ እና የወደብ ልዩ መብቶች ሰረዘች፤ በሀገራቱ መካከል ያለው አይሏል
ይህ የአፀፋ እርምጃ ፓሪስ የአልጄሪያ ዲፕሎማቶች በፈረንሳይ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ለመገደብ እያሰበች ነው ከተባለ በኋላ የመጣ ሲሆን ፈረንሳይ ቀደም ሲል የ80 የአልጄሪያ ባሥልጣናትን ዲፕሎማሲያዊ መብት ነጥቃለች።
የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፈረንሳይ በዲፕሎማቶቹ ላይ ለፈፀመችው ድርጊት አልጄርስ ተመሳሳይ ምላሽ በመስጠት መብቷ፤ በሀገሪቱ የሚገኙ የፈረንሳይ ኤምባሲ ዲፕሎማቶችን ልዩ መብት እንዳነሳ አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ የአልጄሪያ ኤምባሲ በፓሪስ እየደረሰበት ባለው ተከታታይ መሰናከሎች ምክንያት በአልጄርስ የሚገኘውን የፈረንሳይ ተጠባባቂ አምባሳደር አስጠርቷል።
የግጭቱ መንስኤ
ዲፕሎማሲያዊ አለመግባባቱ ፈረንሳይ በምዕራብ ሳሃራ ለሞሮኮ ሉዓላዊነት እውቅና መስጠቷን ተከትሎ የመጣ ነው። አልጄሪያ የሳሃራዊ አረብ ሪፐብሊክን የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት ትደግፋለች።
የግጭቱ ታሪክ
▪አልጄሪያ የፈረንሳይ ሲቪል ሠራተኞችን እና ዲፕሎማቶችን ያባረረች ሲሆን ፈረንሳይም በተመሳሳይ መልኩ መልስ ሰጥታለች።
▪ፈረንሳይ ለአልጄሪያ ዲፕሎማቶች እና ሲቪል ሠራተኞች አስገዳጅ የቪዛ መስፈርቶችን አስቀምጣለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X