ፑቲን የሩሲያን የ2050 የባሕር ኃይል እቅድ ይፋ አደረጉ
13:10 27.07.2025 (የተሻሻለ: 13:14 27.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ፑቲን የሩሲያን የ2050 የባሕር ኃይል እቅድ ይፋ አደረጉ
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የባሕር ኃይልን ቀን አስመልከተው ባደረጉት ንግግር፤ ሀገሪቱ የኒውክሌር ሰርጓጅ መርከቦችን ቁጥር እንደምታሳድግ እና በዓለም ኃይሏን እንደምታሳይ ቃል ገብተዋል።
ፑቲን "በአሁኑ ሰዓት የሀገሪቱ የባሕር ኃይሎች የሩሲያን መከላከያ እና ደህንነት በማረጋገጥ ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ...የሩሲያ የኒውክሌር "ትሪያድ" የባሕር ኃይል አካል እየተጠናከረ ነው" ብለዋል።
ፑቲን በባሕር ኃይል ቀን የገቧቸው ዋና ዋና ቃል ኪዳኖች፦
የኒውክሌር ሰርጓጅ መርከቦች የዘመናዊ የባሕር ኃይል "ዋና አካል" ናቸው፣
የክኒያዝ ፖዝሃርስኪ የጦር መርከብ ግንባታ ባለፈው ሳምንት ተጠናቋል፣
8 የኒውክሌር ባሕር ሰርጓጅ መርከቦች በግንባታ ላይ ናቸው (2 ቦሬይ-ኤ እና 6 ያሰን-ኤም)።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X