የአፍሪካ ኀብረት እና የሶማሊያ ኃይሎች በሰቢድ-አኖሌ የሽብር ጥቃት አከሸፉ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአፍሪካ ኀብረት እና የሶማሊያ ኃይሎች በሰቢድ-አኖሌ የሽብር ጥቃት አከሸፉ
የአፍሪካ ኀብረት እና የሶማሊያ ኃይሎች በሰቢድ-አኖሌ የሽብር ጥቃት አከሸፉ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 26.07.2025
ሰብስክራይብ

የአፍሪካ ኀብረት እና የሶማሊያ ኃይሎች በሰቢድ-አኖሌ የሽብር ጥቃት አከሸፉ

የአል-ሸባብ ታጣቂዎች ትናንት ማለዳ ከሞቃዲሾ በስተደቡብ ምዕራብ በምትገኘው ሰቢድ-አኖሌ ከተማ በሚገኙ ወታደራዊ ካምፖች ላይ የተቀናጀ ጥቃት ሰንዝረዋል። በፍንዳታ እና ተኩስ የጀመረውን ጥቃት፤ የአፍሪካ ኅብረት እና የሶማሊያ የጋራ ኃይሎች በማክሸፋቸው ታጣቂዎቹ ለማፈግፈግ ተገደዋል።

በሶማሊያ የአፍሪካ ኅብረት ድጋፍና ማረጋጋት ተልዕኮ መረጃ መሠረት በተኩስ ልውውጡ፦

በርካታ ታጣቂዎች ተገድለዋል፣

በተኩስ ልውውጡ ሌሎች ቆስለዋል፣

የተለያዩ መሳሪያዎች ተማርከዋል።

ጥምር ኃይሎች በሰኔ ወር ከአል-ሸባብ* ነፃ በወጡት ካምፖች ቁጥጥራቸውን አስጠብቀዋል። ቀሪዎቹን አሸባሪዎች ለመያዝ ወታደራዊ ዘመቻው ቀጥሏል ሲል ተልዕኮው ገልጿል።

ℹ ይህ ክስተት የጋራ ኃይሉ የአል-ሸባብ ደቡባዊ ክፍል ይዞታን ለማዳከም የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ማጠናከሩን ተከትሎ የመጣ ነው። አል-ሸባብ ዓለም አቀፍ ድጋፍ ያለውን መንግሥት ለመጣል በሚያደርገው ጥረት በሶማሊያ የሚገኙ ወታደራዊ ካምፖችን እና የመንግሥት ተቋማትን በተደጋጋሚ ኢላማ ያደርጋል።

* በሩሲያ እና በርካታ ሀገራት የታገደ አሸባሪ ድርጅት

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0