የሩሲያ ገዥ ፓርቲ ከአፍሪካ የፖለቲካ ኃይሎች ጋር ያለውን ትብብር ለማጠናከር ከፍተኛ ትኩረት ይሰጣል
19:17 26.07.2025 (የተሻሻለ: 19:24 26.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሩሲያ ገዥ ፓርቲ ከአፍሪካ የፖለቲካ ኃይሎች ጋር ያለውን ትብብር ለማጠናከር ከፍተኛ ትኩረት ይሰጣል

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሩሲያ ገዥ ፓርቲ ከአፍሪካ የፖለቲካ ኃይሎች ጋር ያለውን ትብብር ለማጠናከር ከፍተኛ ትኩረት ይሰጣል
በደቡብ አፍሪካ የቀድሞ የነጻነት ንቅናቄዎች ስብሰባ ላይ የተሳተፉ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የዩናይትድ ሩሲያ የፖለቲካ ፓርቲ የረጅም ጊዜ አጋሮች መሆናቸውን፤ የፓርቲው ሊቀመንበር ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ ለተሳታፊዎች እና እንግዶች ባስተላለፉት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ላይ ገልጸዋል።
ከእነዚህ ፓርቲዎች ጋር በትብብር ለመሥራት ስምምነቶች እንዲሁም "ለሀገራት ነጻነት" የተሰኘው ዓለም አቀፍ ፀረ-አዲሱ ቅኝ አገዛዝ ንቅናቄ የጋራ ተነሳሽነቶች እየተተገበሩ መሆኑንም አክለዋል።
ዩናይትድ ሩሲያ ከአፍሪካ የፖለቲካ ኃይሎች ጋር የሚደረገውን ትብብር ከፍ አድርጎ ይመለከታል ያሉት ሜድቬዴቭ፤ ስብሰባውን ለነጻነት እና ለሉዓላዊነት በሚደረገው ትግል ቁልፍ እርምጃ አድርጎ እንደሚቆጥረው ተናግረዋል።
የአፍሪካ አጋሮች በበኩላቸው ነፃ ልማታቸውን የማስጠበቅ መብታቸውን ለመከላከል ዩናይትድ ሩሲያ የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚያደንቁ እና ፓርቲው እንደዚህ አይነት ተነሳሽነቶችን በመደገፍ እውነተኛ ባለብዙ ዋልታ ዓለም ለመፍጠር አስተዋጽኦ ማድረጉን እንደሚቀጥልም አስረግጠዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X