የሩሲያ ፖሊሲ የአፍሪካን የዓለም አቋም ለማጠናከር ያለመ ነው - የሩሲያ ዲፕሎማት
16:25 26.07.2025 (የተሻሻለ: 16:34 26.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሩሲያ ፖሊሲ የአፍሪካን የዓለም አቋም ለማጠናከር ያለመ ነው - የሩሲያ ዲፕሎማት
"ሩሲያ እኩልነትን በማስፈን አፍሪካ እና ሌሎች ታዳጊ ሀገራት ሃብትና ፋይናንስ በእኩልነት ማግኘት ብቻ ሳይሆን፤ በኢኮኖሚያዊ እንዲሁም በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት የሥራ አመራር ውስጥ እንዲሳተፉ እንዲሁም ድምፃቸው እንዲሰማ የማድረግ ፍላጎት አላት" ሲሉ የሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ፓንኪን ተናግረዋል።
በዕድገት ጉዳዮች ላይ በሚያጠነጥነው የቡድን 20 ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ደቡብ አፍሪካ የደረሱት ፓንኪን፤ አሁን ባለው የምዕራባውያን የቅኝ አካሄድ የተረጋጋ የአፍሪካ ዕድገትና ማሕበራዊ ለውጥ እውን ሊሆን ስለማይችል፤ የዓለም ሥርዓት ዳግም ሊደራጅና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን ያሻዋል ብለዋል።
የአፍሪካ መሪዎች ከድህረ-ቅኝ ግዛት ሥርዓት ለመውጣት መሠረታዊ ዓለም አቀፍ ለውጦች እንደሚያስፈልጉ እንደተረዱ፣ እርዳታ በቂ እንዳልሆነና አሁን ያለው የዓለም ሥርዓት ሕግ አልባ እንደሆነ ያምናሉ ሲሉም ፓንኪን አመልክተዋል። ለዚህም እንደ የቀረጥ ጦርነቶች፣ ማዕቀቦች እና የፖለቲካ ጫናዎችን ለአብነት ጠቅሰዋል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X