ኢትዮጵያ ወደብ የማግኘት ፅኑ ፍላጎቷን ሰላማዊ ክልላዊ ውህደት ላይ አጽዕኖት በመሰጠት በድጋሚ አረጋገጠች
15:02 26.07.2025 (የተሻሻለ: 15:04 26.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ ወደብ የማግኘት ፅኑ ፍላጎቷን ሰላማዊ ክልላዊ ውህደት ላይ አጽዕኖት በመሰጠት በድጋሚ አረጋገጠች

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ወደብ የማግኘት ፅኑ ፍላጎቷን ሰላማዊ ክልላዊ ውህደት ላይ አጽዕኖት በመሰጠት በድጋሚ አረጋገጠች
ከሀገሪቱ ሰፊ ሕዝብ እና በፍጥነት እያደገ ካለው ኢኮኖሚ አንጻር ለኢትዮጵያ የባሕር በር ወሳኝ ነው፤ ሲሉ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለመንግሥት የመገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።
🟠 እየሰፋ ለመጣው የኢትዮጵያ የንግድ እንቅስቃሴ የባሕር በር አስፈላጊ ነው ያሉት አምባሳደሩ፤ ይህም ለሀገሪቱ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ እንደሆነና በዕድገትና ልማት፣ ሰላማዊ እንዲሁም በጋራ ጥቅም ትብብር ላይ ተመሥርታ ማሳካት እንደምትፈልግ ገልፀዋል።
ዲና መፍቲ አክለውም የኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ግብ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት እያገኘ መምጣቱን ጠቅሰው፤ ሀገሪቱ የክልላዊ መረጋጋትን ባስጠበቀ መልኩ የባሕር በር ለማግኘት ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ ከጎረቤቶቿ ጋር ሰላማዊ የልማት ትብብር እንደምትፈልግ ገልጸው፤ ጎረቤት ሀገራት የኢትዮጵያን የባሕር በር ፍላጎት በአዎንታዊ መልኩ ሊመለከቱት እንደሚገባ መናገራቸው ይታወሳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X